ዓርብ 6 ኦክቶበር 2017

ከማሥተዋል ማዶ

አምፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት
አይቀየርም!"
☞ አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ
ያውቃሉ ግን እደርቃለሁ ብለው
ሳይፈኩ አይቀሩም ፡፡ ሰውም
ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ
ከመፍካትና ስኬታማ ለመሆን
ከመታተር መስነፍ የለበትም፡፡
ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ
፡፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ
ደመራ ናት ።
☞ አንተ በደመራው ስር ያለህ
አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ
የደመራው ብርሀን ይቀንሳል ፡፡
የቻልከውን ያህል ብራ አንተ
ከነገሮች በላይ ነህ ፡፡ በነገሮች
አትረበሽ ፡፡ አየህ አምፖል
ተቃጠለ ተብሎ ቤት
አይቀየርም ፡፡ አምፖል
ተቃጥሏል ብሎ ቤት
የሚቀይር ሞኝ ነው ፡፡
አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ
አልተሳካም ብለህ ተስፋ
አትቁረጥ ራስህን አታጥፋ ፡፡
ይልቅስ አምፖልህን ቀይር
ችግርህን ተጋፈጠው ፡፡
ጭንቀትህን አስጨንቀው ፡፡
ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል
ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ
ነው ፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ
ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ
ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን
ለመስማት ይገደዳል ፡፡
አሁንም እልሀለው ህይወት
በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን
እወቀው ፡፡በህይወትህ ትላንት
ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን
መቀየር ማስተካከል መሰረዝ
አትችልም ፡፡ የምትችለው
አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ
መስራት ነው ፡፡
☞ "መቀየር የማንችለውን ነገር
መቀበል ማለት ተስፋ
መቁረጥ ማለት ሳይሆን
አቅማችንን የምንችለው ነገር
ላይ ማዋል ማለት ነው ::"
በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን
አቅምህን የምትችለው ነገር
ላይ አውለው ። ደግሞም አንድ
ነገር አስታውስ "በሚያልፍ ቀን
ውስጥ የማያልፈውን
አምላክህን ተመልከት ።

ሠብልዬ