ማክሰኞ 24 ጁን 2014
አደጋ አለዉ
በአሁኑ ሠዐት ከጊዜ ወደጊዜ መልኩን እየቀያየረና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ አንዳንድ አካላት መጥፎ የጎጠኝነት ሥሜትን ቼ ብለዉ በዉር ድንብር የዘረኝነት ፈረሥ መድረሻቸዉን ሳያሥተዉሉት በጭፍን ይጋልቡት ይዘዋል ።
ታዲያማ እኛ
የኛነታችን መገለጫ የሆነዉን አንድነታችንን ሊሸረሽር
የሚችለዉ የዚህ አይነቱ ቀፋፊ ድርጊት ተዋናዮችን አይተን መልካሙን መንገድ የምንመርጠዉ እኛ ግን ወዴት ነዉ ነገሩ? አላማችሁ ምንድን ነዉ ?የያዛችሁት መንገድሥ የት ያደርሳችኋል ? ልንላቸዉ ይገባል አልያ ግን ዘር ቆጥረን እኛም አብረን ከነሡ ካበርን የዚች አገር የወደፊት እጣ ፈንታ በልዩነት በአለመሥማማት ብቻ ይፈታና አንድነታችን ይጠፋል ይህ ከሆነ ደግሞ "አደጋ አለዉ"
"ዘራችን ኢትዮጵያዊነት ነዉ
ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር"
ሰኞ 23 ጁን 2014
ኢትዮጵያዊነት
ሠላም ፍቅር አንድነትን እንዲሁም ነፃነቴን አጥብቄ የምሻ ዘር ሀረጌ ሢመዘዝ ኦሮሞ አማራ ትግሬ ወ .ዘ.ተ ያልሆነ ሁሌም ብሄርን አንግቦ የሚነሳን ዘረኝነት ስቃወም ልክ የማይኖረኝ ዘር ሀረግ ብሄሬም አሸናፊ የሌለዉ ፍቅር የሆነና ብሄርተኝነትና ዘረኝነት ያለዉን ክፋት ካልገባቸዉ በተለየ ከተረዱት እኩል የገባኝ ንፁሕ ኢትዮጵያዊ ነኝ ።
" ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ "
"ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር"