ማክሰኞ 24 ጁን 2014

አደጋ አለዉ

     በአሁኑ ሠዐት ከጊዜ ወደጊዜ መልኩን እየቀያየረና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ አንዳንድ አካላት መጥፎ የጎጠኝነት ሥሜትን ቼ ብለዉ በዉር ድንብር የዘረኝነት ፈረሥ መድረሻቸዉን ሳያሥተዉሉት በጭፍን ይጋልቡት ይዘዋል ።
ታዲያማ እኛ
የኛነታችን መገለጫ የሆነዉን አንድነታችንን ሊሸረሽር
የሚችለዉ የዚህ አይነቱ ቀፋፊ  ድርጊት ተዋናዮችን  አይተን መልካሙን  መንገድ የምንመርጠዉ እኛ ግን ወዴት ነዉ ነገሩ? አላማችሁ ምንድን ነዉ ?የያዛችሁት መንገድሥ የት ያደርሳችኋል ? ልንላቸዉ ይገባል አልያ ግን ዘር ቆጥረን እኛም አብረን ከነሡ ካበርን የዚች አገር የወደፊት እጣ ፈንታ በልዩነት በአለመሥማማት ብቻ ይፈታና አንድነታችን ይጠፋል ይህ ከሆነ ደግሞ "አደጋ አለዉ"
       "ዘራችን ኢትዮጵያዊነት ነዉ

                       ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር"
    

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ