ማክሰኞ 14 ኖቬምበር 2017

ሮበርት ሙጋቤ

በአወዛጋቢነት ከሚታወቁት ሮበርት ሙጋቤ ከበርካታ ቀልዶቻቸው መካከል ጥቂቶቹን እነሆ !!

ከሚስተር በርጫ ገጽ የተገኘ
:
1:- አፍሪካ ውስጥ በስነ-ስርዓት የሚከበረው ማስጠንቀቂያ "battery low !"የሚለው ብቻ ነው።
:
2:- ሴቶች በሙሉ የኤድስ መድሃኒት እስኪገኝ ድረስ የግብረ ስጋ ግንኙነት (Sex) አንፈጽምም ብለው ቢያምጹ ኖሮ፡ ወንዶች በ30 ቀናት ውስጥ መድሃኒቱን ባገኙት ነበር።
:
3:- ናይጄርያን የመሰሉ ብዙ ቋንቋዎች የሚናገር ህዝብ ያላቸው አገሮች፡ ዱዳ (መስማት የተሳነው) ፕሬዝደንት ነው የሚያስፈልጋቸው።
:
4:- አዳምና ሄዋን ቻይናዊያን ቢሆኑ ኖሮ፡ እስካሁን ድረስ ገነት ውስጥ በኖርን ነበር። ምክንያቱም የእጸ በለስ ፍሬውን ትተው እባቡን በበሉት ነበር።
:
5:- ከአንድ ሰው በላይ የምታፈቅር ከሆነ፡ ውስጥህ ያለው ልብ ሳይሆን'memory card' ነው፡
:
6:- አንዳንድ ጊዜ ወደ ኋላ መለስ ብለህ ስትመለከት ከእናትህ በላይ ለሴት ልጅ ገንዘብ የምታጠፋ ከሆነ ያኔ እጀ-ሰብ እውነት መሆኑ ይገባሃል።
:
7:- አንዳንድ ሴቶችን ስትመለከት ጂም የሚሰሩ ይመስላሉ። ግን የጂምናዝየምን በር እንኳ አይተውት አያውቁም። ሆኖም ግን ከአንዱ ወንድ ወደ ሌላው ወንድ ለመሮጥ ሲሉ ቅርጻቸውን ይጠብቃሉ።
:
8:- ትዳር እያለህ ከተማሪ ሴቶች ጋር መውጣት ደስ የሚልህ ከሆነ ለሚስትህ የተማሪ ዩኒፎርም ግዛላት፡፡
:
9:- ሰይጣን ራሱ gay አልነበረም፡ ምክንያቱም እራቁቱን ከነበረው አዳም እራቁቷን የነበረችውን ሄዋንን ስለመረጠ፡፡
:
10:- አስቀያሚ ከሆንክ አስቀያሚ ነህ ስለ ውስጣዊ ውበት አትናገር ምክንያቱም X-ray እያየን አይደለም የምንሄደው፡፡
:
11:- አምላክ ምርጥ ተመራማሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከወንድ ልጅ የጎድን አጥንት ወስዶ ድምጽ ማጉያ (loud speaker) ፈጠረ፡፡
:
12:- ዓለም አፍሪካን በድላታለች……
:
ከአውሮፓ አንድ ነጭ ወደ አፍሪካ ከመጣ የውጪ ዜጋ ጎብኚ ይባላል።
:
ከአፍሪካ አንድ አፍሪካዊ ወደ አውሮፓ ከሄደ ግን ህገ ወጥ ስደተኛ ይባላል፡፡
:
በግሩፕ ነጮች ወደ አፍሪካ ከመጡ ቱሪስት ይባላሉ፡፡ በብዛት አፍሪካዊያን ወደ አውሮፓ ከሄዱ ደግሞ ረፍዩጂስ (ስደተኞች) ይባለሉ።
:
ነጮች አፍሪካ ውስጥ መጥተው የአፍሪካዊያን አሰሪ ይሆናሉ፡፡ አፍሪካዊያን አውሮፓ ሄደውም የነጮች ሰራተኛ ነው የሚሆኑት……
:
:
ስለዚህ ዓለም በአፍሪካ ላይ ፍትሓዊት እንዳልሆነች በዚህ እንረዳለን፡፡
:
:

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ