#የሠላም_ሠዉ_ነኝ
ከእንግዲ ዋይታ አይሆንም ወንድም ወንድሙን አይገለዉም
ቃየል በአቤል ላይ አይነሳም ሠይፍ በልብሽ ባንቺ አያልፍምገበሬዉ የጁን አይጣ እርሻዉን ዳዋ አይብላበት
የእናት ቤት ሞሠብ አይጉደል ይሙላልን ጠጋብ በ
ቃየል በአቤል ላይ አይነሳም ሠይፍ በልብሽ ባንቺ አያልፍምገበሬዉ የጁን አይጣ እርሻዉን ዳዋ አይብላበት
የእናት ቤት ሞሠብ አይጉደል ይሙላልን ጠጋብ በ
ሺ እዉነት ቢኖኝ ሺ ምክንያት
አልቆምም ለበደል ለክፋት
ትልቅነት የለም ሠዉ ጥሎ
ያለሠላም ትልቅ ህይወት ጎሎ
አልቆምም ለበደል ለክፋት
ትልቅነት የለም ሠዉ ጥሎ
ያለሠላም ትልቅ ህይወት ጎሎ
#የሠላም_ሠዉ_ነኝ ከተሠኘዉ ዜማ የተቀነጨበ
🔹ወዳጄ ይህን መልካም ሥራ ባልተገባ መንገድ በመቶርጎም የተጠመድን አንዳንድ አካላት በተቻለን መጠን በቀናነትና በመልካም ጎኑ ለመመልከት ብንሞክር መልካም ይመሥለኛል🙏🏽
🔹የሚገርምህ እኮ ወዳጄ ሲጀመር በጣም ብዙ የጥፋት ሥራን የሚሠሩና ህዝቡን ከገንዘቡ አልፈዉ በህይወቱ እየቆመሩ ያሉ ከንቱ ፍጡራን ሳሉ ይህን የዘማሪት ሶፍያን ሽባባዉ ስለ ሀገርና ሥለወገን ሠላም የሚያወሳ ሠናይ ሥራ ለመተቸት መነሳትና ምን ሥም እንደሚሠጠዉ አላዉቅም❓
🔹ምክንያቱም ከርዕሱ አንስተን እሥከ መልእክቱ ዉሥጥ ድረሥ ጠልቀን ብንመለከት ጊዜያችንን ያገናዘበና ድንቅ የሠላምና የፍቅር ሠባኪ ዜማ እንደሆነ እናያለን 👌🏼😍
🔹ወዳጄ እንደኔ እንደኔ አንድ ሠዉ የሠላም ሠዉ ነኝ ብሎ ሌሎችንም ለሠላም ለማነሳሳት ሲጥር ሀሳቡ ከክፋት እሥካልሆነ ድረስ ብንችል ማገዝ መርዳት እና አብሮነትን ማሳየት አልያም ለዚያ ካልታደልን ደግሞ በተቃራኒዉ በመጮህ እራሥን ትዝብት ዉሥጥ ከመክተት ዝም ማለቱ ይሻላል ባይ ነኝ ምክንያቱም ስለሠዉ ልጅ ሠላም መሥበክ ሊያሥመሠግን እንጂ እንደ የሠላም ጠላት እንደመሆን ሊያሥወቅሥም ሥለማይችል ሚናችንን እንለይ🧐
🔹ሥለ ሠላም ሥናይ አይናችን ሊቀላ ሥለ ፍቅር ሥንሠማ ጆሮአችን ሊግል ወይ ለመልካም ተብሎ ለተቋጠረ ሥንኝ በተቃራኒዉ ለመተየብ እጃችንን ከተነሳና አንደበታችንን ከጦር ከሠላ እመነኝ ወዳጄ እዛ ጋር ችግር አለ🔴
🔹ወዳጄ በቃ በአጠቃላይ ምን ለማለት ነዉ ለመልካም ነገር አብረን ልንቆም እንጂ ሊያመን የሚገባ አይመሥለኝም
ዳሩ እንደዉም እኮ ክርሥቶስም ህይወቱን የሠጠዉ ለመላዉ የሠዉ ልጅ ፍቅርና ሠላም ያለ ልዩነት መሆኑንም መዘንጋት ያለብን አይመሥለኝም 🙏🏽
🔹ወዳጄ ይልቅ መልካም ፍሬን እናፈራ ዘንድ መልካም ነገርን መዝራት ሥለሚጠበቅብን ብንችል እኛም ያለ ልዩነት የእዉነትና የፍቅርን ሥብከት አጉልተን እንሥበከዉ ለሠላም እየታገልን በሠላም እንኑር ለፍቅር ሥለፍቅር እየኖርን ለሌሎችም አርአያና የፍቅር ሠዉ እንሁን እላለሁ
🔚በመጨረሻም
👉 ይህ ሀሳብ ከመወገን ወይ ከማንም ጎን ቆሞ ማንንም ለመዉቀሥ በማሠብ ከመንገድ የወጣ እንዳልሆነና ይልቁንም አሁን እየሆነ ካለው እውነት የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋
✍#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት