#ምን_ይበጀን❓
ወዳጄ የሠዉ ልጅ እኮ ሊለካ የማይችል እንዲ እንዲያ ተብሎ የማይገለፅ የመኖሩን ዋሥትና ሆኖ ያለ ሀሳብና ያለ ገደብ በነፃና በነፃነት እንዲተነፍሥ የተቸረዉን ፀጋ የተሰጠዉን ክቡር ነገር በዋጋ የማይተመነዉን ዉድ ገፀበረከት አየር በቀላሉ ዙሪያዉን ከቦት ቢያገኘዉ በገዛ እጁ መርዞ መዉጫ መግቢያ የሚያጣ ምሥኪን ፍጡር ነዉ 😷😭
👉 ወዳጄ ያለ ሀሳብ እንዳሻዉ ይምገዉ የነበር አየር ዛሬ ሥጋቱ ሆኖ 😷 የመኖሩ ምሥጢር የነበረዉን አየር ዛሬ ለመጥፋቱ ምክንያትና እንቆቅልሽ ሲሆንበት ሥታይ �ለምን � ካልክ መልሱ የሚሆነዉ አወቅኩ ብሎ ሲራቀቅ ከፈጣሪዉ ትዕዛዝ ሲያፈነግጥ በገዛ እጁ ነፃነቱን እንዳጣና ክቡር ሥጦታዉን እራሡ እንደበከለዉ ሥተረዳ ታዝናለህ 😷😭
👉ወዳጄ ያለ ገደብ የተሠጠዉን የህይወቱን ምግብ በከንቱ ሥራዉ አቆሽሾ በገደብ ሢጠቀምና እራሡ የራሡን ነፃነት ለማሠር አለመቦዘኑንና አሥሮም ሢጨነቅ ሥታይ ታዝናለህ 😷😭
👉 👨🏻🔬ወዳጄ አሁን ዛሬ ላይ እኔ ነኝ ያለ ሳይንቲስትና ዶክተር አንተንና እኔን ሊያድነን ይቅርና እራሡን እንኳን ማዳን ተሥኖት የጥፋቱ ሠለባ የመሆኑን ዜና ሥትሠማ ትደነግጣለህ🥺
🧐👉ወዳጄ በአለም የተከማቸ ሀብት ገንዘብ ንብረትም ሆነ የረቀቀ ቴክኖሎጂ ችሎ መድሀኒት ሊያሥገኝ አለመቻሉን ሥታይ ትደነግጣለህ😱
#ታድያ_ይበጀን
👇🏽
👉አሟልቶ ሠቶን ሠቶን ጎድለን ሥለተገኘን አክብሮ ፈጥሮን ራሳችንን ሥላረከሥን የሚገባንን ሲሰጠን በማይገባን ሥለተካን የቸርነቱና የምህረቱን ዋጋ ዘንግተን ልካችንን ሥለሳትን አሁን ላይ የሚበጀን ወዳጄ ወደ ፈጣሪ መመለሥና ሥላረግነዉ ክፉ እና ሥለሆነብን ሁሉ ዝቅ ብለን ይቅር ይለን ዘንድ መለመንና ነዉ😭🙏🏽
👉 የመጨረሻ ሳይሆን የመጀመሪያ ምርጫችን መሆን ወደነበረበት ግን በክፋታችን ተጋርደን ወደራቅነዉ መቅረብና ምህረትን እንለምን በሥተመጨረሻዉ ቢሆን የሚበጀን መድሀኒቱም መፍትሄዉም የሚገኘዉ ከርሡ ከፈጣሪ እጅ ነዉና ነዉ እርሡ ይቅር ይለን ዘንድ ዝቅ እንበል። አበቃሁ 🙏🏽 ፈጣሪ ምህረቱን አይንፈገን 🙏🏽
#ዳani_ሞoni_ነኝ_ካለሁበት
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ