እሑድ 10 ሜይ 2020

#ይሄ_ሠዉ_ጀግና_ነዉ

#አንተ_ኢትዮጵያዊ_ነህ

ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ መሠለህ ወዳጄ

* አንዳንድ ሠሞን አንድ ሠዉ "በሚገባዉ" ቦታ ሠዐትና ሁኔታ ላይ ሢወከልና ወዲያዉም በወቅቱ ተፈትኖ የሚመጥን ሆኖ ሲገኝ ሥለገባዉ "አለ" ብለህ ትጠራዋለህ ሥለሚገባዉም "አለልን" ብለህ ትኮራበታለህ ለነገህም በተሥፋ የምጠብቀዉ ሁነኛ ሠዉ እንደሆነ ትናገርለታለህ የኔ ጀግና ሥትልም ትመሠክርለታለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

*የክፋትና የቂም በቀል ታሪኮችን በሚያዋድዱንና አንድ በሚያረጉን ተግባራት እየቀየረ ከትናንት የታሪክ ማህደር ሥንመዝ ለዛሬ መማሪያ ይሆነን ዘንድ እንጂ ለነገ የበቀል መሳሪያ ለማድረግ እንዳልሆነ ተግቶ ሲያስተምር ፍቅርን ሲሰብክ ስታይ የዘረኝነትን ክፋትና ጠንቁ ሥር እንዳይሠድና ዳፋዉ ለትዉልድ እንዳይተርፍ በጥበብ ሲዋጋ ስትመለከት ዛሬ ላይ ነገህን አብርቶ ብሩህ ተሥፋን ሊያሳይህ ሲተጋ ስታይ ንጉሡን ወዳጄ ትገልፀዉ ዘንድ አቅም ያንስህና ሥለ እዉነት በቃ ዝም ትላለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

*በቃ ምን አለፋህ ወዳጄ ሀገርህን ሥሟን በመልካም ሥላወሳ ብቻ ሥሙን በፍቅር ቀለም በልብህ ታትመዋለህ ከመልካም ሥሞች ተርታ ትመድበዋለህ ሥላከበራት ኢትዮጵያ ከአንገት ሰበር ከወገብህ አጠፍ ከጉልበትህ ሸብረክ ብለህ ካከበራት በላይ ታከብረዋለህ ጀግናዬም ትለዋለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

"በቅሎን አባትህ ማነው? ቢሉት ፈረስ አጎቴ ነው" ይላል እንዲሉ ጊዜአችን ያላገናዘቡና በሠነፍ የዘር ፖለቲካ እሳቤያቸዉ አቅላቸዉን የሳቱ የብጥብጥ ሀሳዊ ነብያቶቹ ጠባቡና ጥጋቡ ላይግባቡ ተጋብተዉ የጥላቻ አሥተምህሯቸዉን በ40 መንገድ እየመነዘሩ ትንሽነታቸዉ የማሳነስ ወግ እንዲያወጉ ብታሥገድዳቸዉ ከማይገባቸዉ ጥግ ቆመዉ ትንቢታቸዉ አገር ለማሸበር ህዝብን እስከመቅጠር ሲደርስና የአርግ አታርግ የሁን አትሁንና የአበቃልህ ቀጠሮን ባዘለ ሥካር ናዉዘዉ ሲቅበዘበዙ" ንጉሱ አይቶና ተረድቶ በጊዜ ለኩሉ ጥበብ በማሥተዋል ሲያልፍ ስታይ ወዳጄ ትደመማለህ እኮ ነዉ የምልህ ታዲያ ያኔ ይህን በሳል መሪ የኔ ጀግና ትለዋለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

እናም እኔም እልሀለዉ የዚህን ግሩም መሪ ለሀገርህና ለሀገሬ ያለዉን መልካም ሀሳብ ተረድተህ የራዕዩን የህልሙን ታላቅነት ተገንዝበህ ሥለምትደግፈዉና ከጎኑ በመቆምህ ብቻ የኔ ጀግናዬ ነህ
የዶክተር ወዳጄ ነህ ማህረነን ውብ ሀሳብ ልዋስና አዎን "የአፍሪካ አልማዝ" ሀገሬ ከአሁኑ ጭንቅና ጥብ በኋላ የከበባት ሀዘን ሁሉ ይሸሻል ያደፈው የድህነት ካባዋ ወልቆ በፍቅር በአንድነት ፀዐዳ የክብር ካባ ይቀየራል እንቆቅልሾቿም በሙሉ ተፈተው እምዬ ኢትዮጵያ *የአፍሪካ አልማዝ* ሆና የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም !😍


🔚በመጨረሻም
👉 ይህ ሀሳብ ከመወገን ወይ ከማንም ጎን ቆሞ ማንንም ለመዉቀሥ ወይም ለማወደሥ በማሠብ የተሠናዳ እንዳልሆነና ይልቁንም ጊዜን ተንተረሶ ካለው እየሆነ ካለዉ እውነታ የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋

@ዳaniሞoni ነኝ ካለሁበት

ቅዳሜ 9 ሜይ 2020

#መሥከረም_30


👉🏽ወዳጄ "የፖለቲካ ውይይት ሆነ ድርድር ቢደረግ የሚለው ሃሳብ እንደ ሀሳብ "ጤነኛና ጠቃሚ ጉዳይ ሆኖ የሚታይ መሆን ያለበት ቢሆንም " ዳሩ ግን ማን ከማን ይደራደራል ድርድሩሥ በምን መልኩና እንዴት መሆን አለበት አሁን ላይ ጊዜዉና 😷 ሁኔታዉ አመቺ ነዉ ወይ የሚለዉና ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎችንም አገናዝቦ መሆን ይኖርበታል ።

👉🏽 ግና ከሁሉ በፊት ዋናዉ ጉዳይ ወዳጄ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉም ልደራደር ባዩ ወይም የተደራዳሪዉ አካል "የአዕምሮ ጤንነትም" ከግንዛቤ መግባትም ይኖርበታል‼️🔚 ለምን እንዲ አልክ ብለህ እንደማትጠይቀኝ አሥባለሁ ምክንያቱም  የዚህችን ሀገር አንዳንድ ምሁር ነኝ ባዮች ከምሁራኑ ለመለየት ከባድ በመሆኑና አዕምሮው በእዉቀት የተሞላዉንና በጥበት የጨለለዉን ወይም የጨቀየዉን መለየት ሥለሚያሥፈልግ ነዉ አለበለዛ ግን ሀሳቡም ሆነ ሂሳቡም በመጨረሻ ለፍቶ መና እንዲሉ ለማንም ለምንም በማይበጅ ከንቱ አሉባልታ ይታጨቅና "ያለን እንዳለን ሆኖ" የሠላም መንገድ ዘግቶ ለማይሆን ተጨማሪ መቃቃር በር ከፋች ይሆናል እንዲያም ሲል ወደ ዘላለማዊ ክርክርና ብጥብጥ ካልሆነ በቀር ለህዝቡ የሚፈይደዉ አንዳች ነገር አይኖርም🥺

👉🏽 ቅሉ ግን እኮ ወዳጄ የጥጋቡና ጠባቡ የስሌት እይታ አሁን ላይ ሀገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ በአንፃራዊነት ካለማገናዘቡ አልፎ ለህዝቡ ያላቸዉን የንቀት ጥግና አሥበዉለት ሳይሆን አሥበዉበት የሚጎነጉኑትን ክፋት የሚያሳይ ሆኖ ሥታገኘዉ ትደነግጣለህ 😳

👉🏽 የነ ጥጋቡና ጠባቡ ልካቸዉን ያለማወቅ ክፋቱ ደግሞ ወዳጄ ሀገሪቷን ልክ እንደ ቤታቸዉ ቴሌቪዥንና ህዝቡን እንደ መዝናኛ ቻናል መቁጠራቸዉ ነዉ ብቻ ምን ልበልህ በእጃቸዉ በያዙት ሪሞት ባሻቸዉ ሠዐት የፍቅር ሲላቸዉ የጦርነትን ጣቢያ እየመረጡ እንደፈለጉ የሚቀያይሩትና መሽቶ በነጋ ቁጥር አዉቅልሀለሁ እያሉ ሲያሻቸዉ ድምፁን አፍነዉ🤐 ሳይሾማቸዉ ራሳቸዉን በጠበቃነት ሹመዉ የሚናገሩለት🤗 ሊያዉም ደግሞ ቀድሞ ለተቆራኛቸዉ ያልተገራ የሥልጣን ጥም ማርኪያነትና የአመፅ ቀጠሮን እያስያዙ ለመስዕት በግነት የሚያዘጋጁት አድርገዉ ማሠባቸዉ ነዉ 🧐

ወዳጄ የሆነዉ ሆኖ ግን አሁንም ጠባቡና ጥጋቡ ርዕስ አልባ የጥሪ ካርዳቸዉ ከመበተን አልቦዘኑም ያዉ ሊያደርጉት ያሠቡትና ማን አክብሮ ታዳሚያቸዉ እንደሚሆን ባይታወቅም ማለት ነዉ👉⁉️
እንደኔ እንደኔ ግን ጋሽ ጠባቡን በልክ ሁን ሠከን በል ጥጋቡንም በህግ አምላክ ረጋ በል እያልኩ በማሥተዋል በእዉቀት መጓዝ አርነት ያወጣል እላለሁ

በተረፈ መሥከረም 30🤗 እንገናኝ አበቃሁ🙏🏽

#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት