ቅዳሜ 9 ሜይ 2020

#መሥከረም_30


👉🏽ወዳጄ "የፖለቲካ ውይይት ሆነ ድርድር ቢደረግ የሚለው ሃሳብ እንደ ሀሳብ "ጤነኛና ጠቃሚ ጉዳይ ሆኖ የሚታይ መሆን ያለበት ቢሆንም " ዳሩ ግን ማን ከማን ይደራደራል ድርድሩሥ በምን መልኩና እንዴት መሆን አለበት አሁን ላይ ጊዜዉና 😷 ሁኔታዉ አመቺ ነዉ ወይ የሚለዉና ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎችንም አገናዝቦ መሆን ይኖርበታል ።

👉🏽 ግና ከሁሉ በፊት ዋናዉ ጉዳይ ወዳጄ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉም ልደራደር ባዩ ወይም የተደራዳሪዉ አካል "የአዕምሮ ጤንነትም" ከግንዛቤ መግባትም ይኖርበታል‼️🔚 ለምን እንዲ አልክ ብለህ እንደማትጠይቀኝ አሥባለሁ ምክንያቱም  የዚህችን ሀገር አንዳንድ ምሁር ነኝ ባዮች ከምሁራኑ ለመለየት ከባድ በመሆኑና አዕምሮው በእዉቀት የተሞላዉንና በጥበት የጨለለዉን ወይም የጨቀየዉን መለየት ሥለሚያሥፈልግ ነዉ አለበለዛ ግን ሀሳቡም ሆነ ሂሳቡም በመጨረሻ ለፍቶ መና እንዲሉ ለማንም ለምንም በማይበጅ ከንቱ አሉባልታ ይታጨቅና "ያለን እንዳለን ሆኖ" የሠላም መንገድ ዘግቶ ለማይሆን ተጨማሪ መቃቃር በር ከፋች ይሆናል እንዲያም ሲል ወደ ዘላለማዊ ክርክርና ብጥብጥ ካልሆነ በቀር ለህዝቡ የሚፈይደዉ አንዳች ነገር አይኖርም🥺

👉🏽 ቅሉ ግን እኮ ወዳጄ የጥጋቡና ጠባቡ የስሌት እይታ አሁን ላይ ሀገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ በአንፃራዊነት ካለማገናዘቡ አልፎ ለህዝቡ ያላቸዉን የንቀት ጥግና አሥበዉለት ሳይሆን አሥበዉበት የሚጎነጉኑትን ክፋት የሚያሳይ ሆኖ ሥታገኘዉ ትደነግጣለህ 😳

👉🏽 የነ ጥጋቡና ጠባቡ ልካቸዉን ያለማወቅ ክፋቱ ደግሞ ወዳጄ ሀገሪቷን ልክ እንደ ቤታቸዉ ቴሌቪዥንና ህዝቡን እንደ መዝናኛ ቻናል መቁጠራቸዉ ነዉ ብቻ ምን ልበልህ በእጃቸዉ በያዙት ሪሞት ባሻቸዉ ሠዐት የፍቅር ሲላቸዉ የጦርነትን ጣቢያ እየመረጡ እንደፈለጉ የሚቀያይሩትና መሽቶ በነጋ ቁጥር አዉቅልሀለሁ እያሉ ሲያሻቸዉ ድምፁን አፍነዉ🤐 ሳይሾማቸዉ ራሳቸዉን በጠበቃነት ሹመዉ የሚናገሩለት🤗 ሊያዉም ደግሞ ቀድሞ ለተቆራኛቸዉ ያልተገራ የሥልጣን ጥም ማርኪያነትና የአመፅ ቀጠሮን እያስያዙ ለመስዕት በግነት የሚያዘጋጁት አድርገዉ ማሠባቸዉ ነዉ 🧐

ወዳጄ የሆነዉ ሆኖ ግን አሁንም ጠባቡና ጥጋቡ ርዕስ አልባ የጥሪ ካርዳቸዉ ከመበተን አልቦዘኑም ያዉ ሊያደርጉት ያሠቡትና ማን አክብሮ ታዳሚያቸዉ እንደሚሆን ባይታወቅም ማለት ነዉ👉⁉️
እንደኔ እንደኔ ግን ጋሽ ጠባቡን በልክ ሁን ሠከን በል ጥጋቡንም በህግ አምላክ ረጋ በል እያልኩ በማሥተዋል በእዉቀት መጓዝ አርነት ያወጣል እላለሁ

በተረፈ መሥከረም 30🤗 እንገናኝ አበቃሁ🙏🏽

#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት

1 አስተያየት:

  1. ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡

    ምላሽ ይስጡሰርዝ