ረቡዕ 4 ኖቬምበር 2020

#እባካችሁ

እባካችሁ

አረ ምን አይነት በሽታ ነዉ  ግን የተቆራኘን   ወገኔ እንዴ በዚህ ክፉ ቀን እርሥ በርሥ ተከፋፍለን እየከፋፋን መጋደላችን ሳይበቃን እንደገና እንደመልካም ነገር  በህይወት የተለዩ ወገኖችን ምሥል በማህበራዊ ሚዲያ እየለቀቅን የምንሳለቀዉ ነገር አረ ምንድን ነዉ ?

     አረ በፈጣሪ ጭካኔያችን በልክ ይሁን ባያድለን እነጂ እኮ ሟችም ገዳይም ጦርን የሚሠብቁት ለጠላት  እንጂ እርሥ በርሥ ባልነበር ዳሩ ምን ይሆናል የቀን ጎዶሎ ለፖለቲካ ቁማር እንዲመች በመሀከላቸዉ ቅራኔን ፈጥረዉ እርሥ በርሥ እንጢጠፋፉ አዘጋጇቸዉ ተጋደሉ 

     ወገኔ በዚህ መከፋፋት አትራፊ የለም አሸናፊ ተሸናፊም የለም ዛሬ ትርፍ ለሌለዉ መሥዋዕትነት ህይወቱን ያጣዉ ወታደር እኮ እንዳተዉ ምሥኪን ደሀ እናትና አባት አሉት እንደዘበት እንደቀልድ ፖሥት የምታረገዉ የአሥክሬን ፎቶ ልታሥበዉ  ከምትችለዉ በላይ ከባድ ጥፋትን ያሥከትላል 

እባካችሁ እባካችሁ ዘግናኝ  ምሥሎችን አትልቀቁ

@dኒmoኒ

በፖለቲካ

"በፖለቲካ ውሰጥ ምንም ነገር በድንገት አይፈጠርም፣ 
ድንገተኛ ነገር እንኳ ቢፈጠር፣ ነገሩ ድንገተኛ እንዲመስል ተደርጎ #ስለመታቀዱ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።" 
          - ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት

https://www.facebook.com/179943078867733/posts/1405744026287626/

#የትግራዋይ_እናት

እኔ ግን የትግራይ እናት ታሳዝነኛለች እድሜ ልኳን ልጆቿን በጦርነት እንደተነጠቀች እንደገበረች 
     ጥቂት አካላት የፖለቲካ ስልጣን ወንበራቸዉን አንቀዉ ሲቆምሩ   የምሥኪን እናት  ልጆችን እርስ በርስ  ያዋጓቸዋል እርሥ በርሥ   ያጨካክኗክኗቸዋል ወንድም ወንድሙን ገሎ ጀግና ላይባል ለናቱ የዘላለም ሀዘንን ከማዉረሥና ለራሡም ፀፀት ከማቆየት በቀር ትርፍ የለዉም 
ሀዘናችን በዛ ፈጣሪ በቃችሁ ይበለን 😭

@ዳaniሞoni