ማክሰኞ 17 ጁን 2025

#ፍቅር

 

#እዉነተኛ_ፍቅር

ፍቅሩ ታመመችበት ይሆነዉ አጣ  ለሀኪም ሊደዉልም ሥልኩን አነሳ
ነገር  ግን  ዉዱ ሀኪም  አትጥራ እጅህን በእጄ እነደያዝኩ 😍🤝🏼 በደሥታ በሰላም መተኛት እፈልጋለሁ አለችዉ አይሆንም ብሎ ለመደወል
ቢያንገራግርም ለመነችዉ እርሡም ፍላጎቷን ሊነፍጋት አልተቻለዉም ምክንያቱም ከራሡም አብልጦ ይወዳታልና ።

እንዲያዉዉ

ያለፈውን የፍቅር ቀናቶች እንዴት እንደተገናኙ እጁን በእጇ እንደያዘ😍🤝🏼 ያወሡ ጀመር  አሁንን እያሠቡ እነሱ አላለቀሱም ይልቁንም ባሳለፉት ደማቅ ቀናት ወደኃላ እየተጓዙ ፈገግ አሉ ፡፡ እነሡ አልተጸጸቱም ለነበራቸዉ ጊዜ  አመስጋኞችም👩‍❤️‍👨🙏🏽 ነበሩ ፡፡

እርሷም  ከፊቷ ተንበርክኮ🧎🏾‍♂️ በሥሥት ለሚመለከታት የልቧ ንጉሥ😍🤴🏾 በህመም በታፈነ ድምፅዋ እየታገለች  በድጋሜ በድጋሜ ማብቂያ በሌለዉ ፍቅር  “ለዘላለም እወድሀለሁ” አለችዉ።
እርሡም ለዉዱ ቃላቶችን መምረጥና ማዉጣት ለእርሷ ለልቡ ንግሥትም 😍👸🏼የገዘፈ ፍቅሩን መግለፅን ቢሳነዉ ጠጋ  ብሎ  ግንባርዋን ላይ በፍቅር  ስሞሽ ሳማትና ተመልሶም አይኖቹን በአይኖቿ ላይ ጥሎ በጥልቅ ዝምታ ተዋጠ  💞

ከገደብ ያለፈ የፍቅሩን ልክ  ከዝምታዉ ጥልቀት በላይ  ከአይኖቹ   የተረዳች እርሷም በደሥታና  በፈገግታ  ፊቷ እንዳበራ እጁን በእጇ እንደያዘች  አይቿን ጨፈነች  በሰላም አንቀላፋች ፡፡💔

"ማንም  ሰው ቢሆን   ወደዚች ሲመጣ አለም ከፍቅር በስተቀር  ምንም ነገር የለዉም እንደገናም ደግሞ  ወደማይቀርበት አለምም ሲሸኝ ከፍቅር በስተቀር ምንም ነገርን አይተወውም ፡፡"  በፍቅር እንኑር

@ እዳaniሞoni

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ