ማክሰኞ 17 ጁን 2025

#ፍቅር

 

#እዉነተኛ_ፍቅር

ፍቅሩ ታመመችበት ይሆነዉ አጣ  ለሀኪም ሊደዉልም ሥልኩን አነሳ
ነገር  ግን  ዉዱ ሀኪም  አትጥራ እጅህን በእጄ እነደያዝኩ 😍🤝🏼 በደሥታ በሰላም መተኛት እፈልጋለሁ አለችዉ አይሆንም ብሎ ለመደወል
ቢያንገራግርም ለመነችዉ እርሡም ፍላጎቷን ሊነፍጋት አልተቻለዉም ምክንያቱም ከራሡም አብልጦ ይወዳታልና ።

እንዲያዉዉ

ያለፈውን የፍቅር ቀናቶች እንዴት እንደተገናኙ እጁን በእጇ እንደያዘ😍🤝🏼 ያወሡ ጀመር  አሁንን እያሠቡ እነሱ አላለቀሱም ይልቁንም ባሳለፉት ደማቅ ቀናት ወደኃላ እየተጓዙ ፈገግ አሉ ፡፡ እነሡ አልተጸጸቱም ለነበራቸዉ ጊዜ  አመስጋኞችም👩‍❤️‍👨🙏🏽 ነበሩ ፡፡

እርሷም  ከፊቷ ተንበርክኮ🧎🏾‍♂️ በሥሥት ለሚመለከታት የልቧ ንጉሥ😍🤴🏾 በህመም በታፈነ ድምፅዋ እየታገለች  በድጋሜ በድጋሜ ማብቂያ በሌለዉ ፍቅር  “ለዘላለም እወድሀለሁ” አለችዉ።
እርሡም ለዉዱ ቃላቶችን መምረጥና ማዉጣት ለእርሷ ለልቡ ንግሥትም 😍👸🏼የገዘፈ ፍቅሩን መግለፅን ቢሳነዉ ጠጋ  ብሎ  ግንባርዋን ላይ በፍቅር  ስሞሽ ሳማትና ተመልሶም አይኖቹን በአይኖቿ ላይ ጥሎ በጥልቅ ዝምታ ተዋጠ  💞

ከገደብ ያለፈ የፍቅሩን ልክ  ከዝምታዉ ጥልቀት በላይ  ከአይኖቹ   የተረዳች እርሷም በደሥታና  በፈገግታ  ፊቷ እንዳበራ እጁን በእጇ እንደያዘች  አይቿን ጨፈነች  በሰላም አንቀላፋች ፡፡💔

"ማንም  ሰው ቢሆን   ወደዚች ሲመጣ አለም ከፍቅር በስተቀር  ምንም ነገር የለዉም እንደገናም ደግሞ  ወደማይቀርበት አለምም ሲሸኝ ከፍቅር በስተቀር ምንም ነገርን አይተወውም ፡፡"  በፍቅር እንኑር

@ እዳaniሞoni

ቀድሜ ባውቃቸው ኖሮ ያልኳቸው 10 ምክሮች 👌


♻️መዝናናት ማለት መጠጣት፣ ፓርቲ ማድረግ እና ከሰው ጋር መዋል ብቻ አይደለም። መዝናናት ማለት ብቻህን የምታሳልፋት ምሽት፣ መጽሐፍ ውስጥ ሰምጦ ማንበብ፣ ጥልቅ ውይይት ማድረግ、እርምጃ መውሰድ፣ ስነ-ጥበብ መፍጠር፣ ሙዚቃ መጫወት ወይም ስራህን መስራት ሊሆን ይችላል። መዝናናት ያንተ ነው፤ ትርጉሙን የምትሰጠው አንተው ራስህ ነህ።

♻️"እምቢ" ለማለት ብዙ ማብራሪያ መስጠት እንደሌለብህ እወቅና ልማድህ አድርገው።

♻️ለግል ድንበርህ/ወሰንህ ክብር የማይሰጥና የሚቀየምህ ሰው ካለ ችግሩ የራሱ ነው። በህይወትህ ውስጥ ልታስወግዳቸው ከምትችላቸው ሸክሞች ሁሉ ትልቁ ሸክም፣ ሌሎች ሰዎች ስለአንተ ያላቸው አስተያየት ነው።

♻️ጓደኛ ታፈራለህ፤ ታጣቸዋለህም። ስህተት ትሰራለህ፤ ታርማለህም። ትወድቃለህ፣ ትከሽፋለህ፣ ትማራለህ፣ ትገነዘባለህ፣ ከእውነታው ጋር ትጋጫለህ፣ በፍቅር ትወድቃለህ፣ ትጎዳለህም። ራስህን ታጣለህ፤ በመጨረሻም ትጠነክራለህ።

♻️99% የሚሆነው ጉዳት በአዕምሮህ ውስጥ በአንተና በአስተሳሰብህ የሚፈጠር ነው። 1% የሚሆነው ጉዳት ብቻ ነው በእውነተኛው ሁኔታና በውጤቱ የሚከሰተው።

♻️የአዕምሮ ምግብህን አሻሽል።

የአኗኗር ስርአትህ የምትመገበው ብቻ እንዳልሆነ ስትገነዘብ ሁሉም ነገር ይለወጣል። የአኗኗር ስርአትህ የምታየው፣ የምታነበው፣ የምትከታተላቸው ሰዎች እና አብረሃቸው ጊዜ የምታሳልፋቸው ጭምር ነው። ግብህ ጤናማ አዕምሮ እንዲኖርህ ከሆነ፣ ከአዕምሮ ምግብህ ላይ "ቆሻሻ ምግቦችን" ማስወገድ ጀምር።

♻️የምትወደውን ሰው ለመማረክ ብቻ አካላዊ ውበትህ ላይ ብዙ ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ አዕምሮአዊ ውበትህን በማሳደግ ላይ አተኩር። ራስህን አስተምር፣ ተደጋጋሚ መርዛማ አስተሳሰቦችህን ተጋፈጣቸው፣ የበታችነት ስሜትህን አስተካክል እና በራስህ ደስተኛ መሆንን ተማር።

♻️ብዙውን ጊዜ ችግሩ ራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ ስለ ችግሩ የምታስብበት መንገድ ነው። አብዛኛውን ችግሮችህን አስተሳሰብህን በማስተካከል ብቻ መፍታት ትችላለህ።

♻️ከማግባትህ በፊት፣ ስለ ገንዘብ አጠቃቀም፣ ስለ ልጅ አስተዳደግ፣ ልጆቻችሁ በምን አይነት እምነት ማደግ እንዳለባቸው፣ ስለ ልጅነት የስነ-ልቦና ጠባሳዎች፣ ስለ ወሲብ ያላችሁ ምልከታ、ስለ ገንዘብ ነክ ምልከታዎች፣ ስለ ቤተሰብ የጤና ታሪክ፣ ስለ ህልም ቤት፣ ስራና ትምህርት እንዲሁም አዕምሮአችሁ ውስጥ ስለሚመጡ ማናቸውም ነገሮች ተወያዩ።

ፍቅር ብቻውን በቂ አይደለም።

ልጆችህ አንተን ወላጅ በማግኘታቸው ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመፈወስ እንዳይገደዱ፣ ልጆች ከመውለድህ በፊት አንተ ከውስጥ ቁስሎችህ ተፈወስ።

♻️ራስህን ታጣለህ፤ በመጨረሻም ትጠነክራለህ። አስታውስ! እነዚህ የህይወትህ ምርጥ ዓመታት ናቸው። በነዚህ ዓመታት በመደሰት እና እነሱን በማበላሸት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት አለብህ።
©ተዋነይ 

#ውብ #ቀን ❤