አድዋ
የሰው ልጅ ክቡር ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሊያከበር::
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ በክብር ይሄዳል
ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል፡፡
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነጻነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደም እና ከአጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነጻነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር፡፡
ትናገር አድዋ ትናገር ሃገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፡፡
በኩራት በክብር
በደስታ በፍቅር
በድል እኖራለው ይኀው በቀን በቀን
ደግሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፡፡
ምስጋና ለነሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነጻነት ላበቁኝ ወገኖች፡፡
የጥቁር ድል አምባ አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ…!!!
አዎ ተናገሪ ተናገሪ
የድል ታክሽን አውሪ፡፡
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሊያከበር::
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ በክብር ይሄዳል
ሰው ሊኖር ሰው ሞቷል፡፡
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነጻነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደም እና ከአጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነጻነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር፡፡
ትናገር አድዋ ትናገር ሃገሬ
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፡፡
በኩራት በክብር
በደስታ በፍቅር
በድል እኖራለው ይኀው በቀን በቀን
ደግሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፡፡
ምስጋና ለነሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነጻነት ላበቁኝ ወገኖች፡፡
የጥቁር ድል አምባ አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ…!!!
አዎ ተናገሪ ተናገሪ
የድል ታክሽን አውሪ፡፡
በእጅጋየው ሽባባው