እሑድ 27 ዲሴምበር 2015

ቅጠል እየበጠስሽ ስትጥይ አይቻለሁ

በአንድ ወቅት ባልና ሚስት የጦፈ ጭቅጭቅ ውስ
ናቸው የጭቅጭቃቸው መንስኤ ደግሞ የባል ደከማና ማየት
የተሳናቸው እናት ነበሩ ታዳ ሚስቲቱ የባሏን እናት ቤት ውስጥ
አስቀምጦ መጦሩን አልወደደችም ነበር:: በዚህ የተነሳው
መቇጫ ያላገኘውን
ጭቅጭቅ እኔን ወይም እናትህን ምረጥ በሚለው በሚስት
ተብየዋ የመጨረሻ ንግግር ረገብ አለ!...... ባልም አውጥቶ
አውርዶ,,,, ቇጥሮ ከፈታ ቡሃላ ሚስቱን መረጠ እናም ከሚስቱ
ጋር ተመካክሮ ራቅ ብሎ ከሚገኘው ጫካ ውስጥ እናቱን
ለመጣል ወሰነ.... ወስኖም አልቀረ እናቱን አዝሎ ወስዶ ጫካ
ውስጥ ጥሏቸው ተመለሰ:: ታዳ በዚህ
ጊዜ እውነታውን ሲከታተል የነበረ አንድ ሽፍታ ወደ እናትየዋ
ተጠግቶ እንዲህ አላቸው <<ልጅሽ እዚህ አስፈሪ ጫካ
ውስጥ
ጥሎሽ ተመለሰ ነገር ግን አዝሎ ሲያመጣሽ ጀርባው ላይ
ሆነሽ
ቅጠል እየበጠስሽ
ስትጥይ አይቻለሁ
ለምንድን ነበር እንደዛ ያደረግሺው>> ብሎ ሲጠይቅ እናትም
እነዲህ አሉት <<ልጄ እኔን ጥሎኝ ሲመለስ መንገዱ ጠፍቶት
አውሬ እንዳይበላብኝ ምልክት እንዲሆነው ነው>> ብለው
መለሱለት..... እናት ለዘላለም ትኑር

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ