ሞባይል አጠቃቀማችን እየገደለን ነው
• በተለይ ለወንዶች ሞባይሉን በፊት ለፊት የሱሪ ኪስ ውስጥ ወይም በብልታቸው በሚቀርብ ሁኔታ አይያዙ፡፡ ጨረሩ ሲደጋገም ለመሀንነት ያጋልጣል፡፡
• ሞባይሎን ኪስዎ ውስጥ የሚያደርጉ ከሆነ ወይም በወገብ የሚታጠቁት ከሆነ ኪፖድ ወይም የቁጥር ቁልፎችን ወደ ሰውነትዎ አቅጣጫ ያድርጉ፣ ማለትም የስፒከሩ ፊት ወደ ውጭ ይሁን፣ ምክንያቱም ስልክ ሲደወል ጨረሩ በስፒከሩ በኩል ስለሚለቀቅ ወደ ሰውነትዎ ሳይሆን ወደ አየሩ ይበተናል፡፡ ወደ ሰውነት የመግባት እድሉ አነስተኛ ነው፡፡ ጠረጴዛ፣ አልጋ፣ ወንበር….ወዘተ ላይ ሲያስቀምጡትም ስፒከሩ ወደ መሬት አቅጣጫ፣ ቁጥሩ ደግሞ ወደ ላይ ይሁን፡፡
• ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ፡፡ ቢያንስ ከ5 ሳንቲ ሜትር በላይ ራቅ ማድረግ ኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲየሽን ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡
• ሞባይሎን ታቅፈው አይተኙ፡፡ በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 ሜትር ያርቁት፡፡ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው ኤሌክትሮማግኔትክ ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ፡፡
• ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፡፡ የጽንሱ ሕዋሳት ለኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽን እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው፡፡ ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን፡፡ አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቆሎ መደዋወል መቀነስ አለበት፡፡
• ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል አይጠቀሙ፡፡ ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል፡፡ ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ፡፡ የሚጠቀሙም ከሆነ በአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡
• በተለይ! በተለይ!!! ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል፡፡ ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡
• በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው፡፡ ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
• አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው፡፡ ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ይሰርፃል፡፡
• ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት፡፡
• የባትሪ ቻርጅ በጣም ሎው ሲሆን፣ ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ፡፡ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል!
-‹‹የዕውቀት ማኅደር›› (2005)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ