♦️ #የ200_ሺ_ጉድጏዱ_ነገር_ዉሸትም_ሆነ_እዉነት_ወሬውንለባለቤቱና_ፍርዱንም_ለህግ_ሰዎች_ትተን_ግድ_ካልሆነብን_በቀር_ከቤት_ባለመዉጣት_እራስህንና_ሌሎችን_እጠብቅ🙏🏽
#በጥያቄ_ልጀምርና 🤔ወዳጄ 200 ሺ ጉድጏድ ምናምን እያሉ ወሬ የሚያራቡና የሚያራግቡ የጠባቡና ጥጋቡ ደቀመዛሙርትን ምን ትላቸዋለህ ❓
➖እንደ እኔ ከሆነ ባልተረጋገጠ ወሬ ይህን ምስኪን ህዝብ ከበሽታዉ በላይ ጭንቀት ከምታበዙለት ይልቅ እባካችሁ ብትችሉ አፋችሁን ዝጉ አልያም ልሳናችሁን ለማስተማሪያነት ተጠቀሙበትና እላለሁ፤🙏🏽
➖በዚህ አሥከፊ ሁኔታ ለሌላ ጊዜያዊ ጥቅምም ከሆነ የምትሮጡት ጥቅማችሁ እዉን የሚሆነዉ ህዝቡ ሢኖር ነዉና ቆም ብላችሁ አሥቡ ዛሬን መልካም ነገሮችን በማረግ ተርፋችሁ አትርፉት ከዛም ነገ ላይ እመኑኝ በእርግጠኝነት ታተርፋላችሁ እላለሁ🙏🏽
♦️ዳሩ ግን እኮ ወዳጄ ህዝቤ በራሡ በተለያዩ አለማት እየሆነ ካለዉ ከሚታየና ከሚሠማዉ ዜና እንኳን የተማረና የበሽታውን አሥከፊነት የተረዳዉ አይመሥለኝም
#ልብ_ብለህ_ከሆነ🔴🧐
👇🏽 👇🏽
👉አፉን አፍንጫዉን 😷�በማስክ ሸፍኖ በእጁ ይጨባበጣል🤝🏼🥺
👉በእጁ ማክስ አርጎ ተቃቅፎ ጉንጭ ጉንጭ ይሳሳማል 😳🥺
👉ለጥንቃቄ የሚጠቅሙ ቁሶችን ለመግዛት የተጨናነቀ ሠልፎችን በፋርማሲዎች ትመለከታለህ😳🥺
👉እጅን መታጠብ መልካም ቢሆንም አንድ ላይ እጅብ ብሎ ሲታጠብ ትታዘባለህ😳🥺
👉ለጥንቃቄ ብሎ ባጠለቀዉ ጓንት ምግብን እያነሳ ሲመገብ ሥታይ ትደነግጣለህ😳🥺
👉ዳሩ አንዳንድ ታዋቂ ሠዎችም የተዛባ መረጃን ከመሥጠት አልፈዉ ታጅበዉ እጅ መታጠብን ሲያስተምሩ በሽታዉ በእጅ ብቻ ሳይሆን በትንፋሽ መተላለፋን መዘንጋታቸዉ ያስገርማል😳🥺
☝🏽👉ይህን ስል በሳል በሆነ መንገድ ለወገን ለመድረስ ርቅት በመጠበቅና ንክኪን በመቀነስና ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ እንዴት ከወረርሽኙ እንደምንጠበቅ ግሩም አሥተማሪ መልዕክቶቾችን ከማስተላለፍ አልፈዉ እዉቅናቸዉን ተጠቅመዉ በጉልበታቸዉ በገንዘባቸዉ ሠዎችንም በማስተባበር ለወገን ደራሽነታቸዉን አርዐያነታቸዉን በግልፅ የሚያሳዩንን አያካትትም ለነሡ በክብር እጅ እነሳለሁ🙏🏽
👉ደሞ ይባሥ ብሎ ይህን ሁኔታ ተገን አድርገዉ አላሥፈላጊ ትርፍን ለማጋበስ ከድሀዉ ለመዝረፍ የሚያሠፈሥፉ ነጋዴዎችን የጭካኔያቸዉ ልክ ሥታይ ደሞ ያምሀል😰 ብቻ ግን በሥንቱን ታዝናለህ መሠለህ ወዳጄ ቅሉ ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ ለጥንቃቄ ብሎ ምሥኪን ወገኔ የሚሄድበትን ርቀት ሳይ ነገን እፈራለሁ 😔🥺
እናም ወዳጄ ሳጠቃልልህ የ200 ሺ ጉድጏዱ ነገር ዉሸትም ሆነ እዉነት ወሬውን ለባለቤቱና ፍርዱንም ለህግ ሰዎች ትተን ግድ ካልሆነብን በቀር ከቤት ባለመዉጣት ከወጣንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛንና የእጅ ጓንቶችን በመጠቀም ከሠዎች ጋር ሥንገናኝ ርቀታችንን በመጠበቅ የ በተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች የሚሠጡትን ትምህርቶች ተግባራዊ በማረግ እራሳችንን ጠብቀን ሌላዉንም እንጠብቅ እላለሁ። አበቃሁ 🙏🏽
#ዳani_ሞoni_ነኝ_ካለሁበት