ሰኞ 28 ኦክቶበር 2019

#በአንድ_ሀገር_ሁለት_መንግስት‼

#በአንድ_ሀገር_ሁለት_መንግስት‼

#ኦርያ_ኢትዮጵያ_ማሔር_ሻላል_ሐሽ_ባዝ"🥺

#የኢትዮጵያ_ተባዮች_ከላይዋ_ላይ_ተነሱ…..#ምርኮ_ፈጥንዋል….#ብዝበዛም_ቸኩሏል "🥺

#አሁን_ላይ
     ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ዘር ቆጠራ "ዘረኝነት ጎልቶ የነፃነት ቀንዲል  የተባለች ሀገር  ኢትዮጵያ በጥቂት ወገኖች ጥጋብ 
 በአደባባይ ተደፍራለች !

#ነፃ_ህዝቦቿ_ቀን_አውጪ_በተባሉ_አካላት_ቀኑ_ጨልሞባቸዋል !🥺

#በአንድ_ሀገር_ሁለት_መንግስት_ሰልጥኖ_ህዝቤ_ተጨንቋል !🥺

👇 
*#ህግ_የማያስከብር_መንግስት 
   #ሰባኪው_ቡድን 
         👉 ይህ አንዱና የላይኛውን ቦታ በስም ብቻ እየታየበት ህግን አላስከበረም ተብሎ   እንዳይወቀስ እያባበለ  ተሽሞንምኖ ሀላፊነትን ለመወጣት ይፍራ ወይ ይለግም ያለየነው  ቅጥ አምባሩ የጠፋብን ቡድን ነው

#ብቻ_ግን_እየሰበከን
 
     *የእምነት ቦታወች ተቃጠሉ ቅርሶች ወደሙና ተዘረፉ     ሰባኪው መንግስት ባላየ አለፈው🥺

*   ባንኮች በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ ተዘረፉ ሰባኪው  መንግስት ባላየ አለፈው🥺

*ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ተዘንግቶ  በጎሳ እየተለዩ የጅምላ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ሰባኪው መንግስት ባላየ አለፈው🥺

*የተማሩ ለሀገር ለወገን እየለፋ የነበሩ በአደባባይ ተገደሉ ሰባኪው መንግስት ባላየ አለፈው 🥺

* ድሆች ከደሳሳ ጎጆቸው እየተፈናቀሉ ሲንገላቱ   ሰባኪው መንግስት ባላየ አለፈው🥺

* ምስኪኑ ህዝብ ከእጅ ወደ አፍ ለሆነ ኑሮው ከሚያገኘው ቀንሶ ቆጥቦ የገነባው የጋራ መኖሪያ የቤት ልጅና የውጭ ይሉትን ብሂል በሚያራምደው ቡድን  በጉልበት ለተረኞች ሲታደል ይህ ሁሉ ሲሆን ሰባኪው መንግስት እያየ ባላየ አለፈው🥺

#ሲከፋም
* ኢትዮጵያዊያን በአደባባይ በመንጋ በድንጋይ ተወግረው በግፍ ሲገደሉ ከአዕምሮ በላይ በሆነ ጭካኔ  ተዘቅዝቀው ሲሰቀሉ   በድናቸው መንገድ ከመንገድ እየተጎተተ እንኳን የሰው ልጅ ሰይጣንን የሚደነግጥበት በደል ሲፈፅሞባቸውና   ከዚህም በላይ እየሆነብን  ሰባኪው መንግስት እየሰበከን እዚ አድርሶናል 🥺🤒🤕

ስለዚ ነው እንግዲ ሲከፋውና ጭቆና የጠናበት ወገኔ              👉🥺" ወይ ውረድ ወይ ፍረድ " የሚል 🥺

👇
#ህግ_የማያከብር_መንግስት 
#የነ_ጥጋቡና_ጠባቡ_አሸባሪ_ቡድን👹

     👉  ይህ ደግሞ ሌላኛው አካል  ከታች ያለ መስሎ ነገር ግን ባሻው ሰዐት ህግን እየጣሰና የንፁኋንን ደም በከንቱ  እንዲፈስ ምክንያት እየሆነ የህዝብ አይን ተብሎ ከጀግና ተቆጥሮ የሚሞካሽና የሚመራቸው መንጋዎች ለሚፈፅሙት ተግባር እውቅና ተሰጥቷቸው  ምስኪኑን ህዝብ ሀገር  የሚያሸብሩ የነ ጥጋቡና ጠባቡ መንግስት ሲሆን
ተግባሩናና ምግባሩ ከላይ የተጠቀስኳቸውንና ሌሎች አሰቃቂ ተግባራትን የሚያስፈፅምና የሚፈፅምና በጉልበት በብዛት የሚያምን 👹አሸባሪ ቡድን👹 ነው ! 

    #ኦርያ_ኢትዮጵያ_ማሔር_ሻላል_ሐሽ_ባዝ"

#የኢትዮጵያ_ተባዮች_ከላይዋ_ላይ_ተነሱ…..#ምርኮ_ፈጥንዋል….#ብዝበዛም_ቸኩሏል 

" እኛ ኢትዮጵያዊያን ሰላም እንሻለን ህግን አክብሮ የሚያስከብር መንግስትን እንሻለን በጥቂት አሸባሪዎች ምክንያት የሰው ህይወት ረክሶ የሞት ዜና እንደ መልካም  ብስራት እየተነገረ ነጋችንን በጭንቀትና በስጋት መኖር ከብዶናል በግፍ ለሞቱት ወገኖቻችን ፍትህ እንሻለን 
ፍትህ !!
ፍትህ!!

#ፍትህ_ለወገኔ!!

👉 ይህ ሀሳብ የክፉዎችን ከመንገድ የወጣ ተግባርና የወገኔን  ስቃይና ሞት ይልቁንም የመንግስትን ቸልተኝነትና ለማውገዝ  ታስቦ አሁን  እየሆነ ካለው  እውነት የተቀዳ  እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም   ማመኑና  ለመፍትሄ  መታገል አይከፋም እላለሁ "👋አበቃሁ

#daኒmoኒ_ነኝ_ካለሁበት

ቅዳሜ 26 ኦክቶበር 2019

#የአፍሪካ_አልማዝ*

*የአፍሪካ አልማዝ*


  


       

     እሷ እኮ ነው በሰዐሊያን ምናብ በጥልቀት  የምትሳል  በገጣምያን የቅኔ ጥበብ ተኩላ በውብ ድምፀት የምትቀነቀን አርማዋ በሰማይ የታተመላት በቅዱስሳን መፀሐፍት በተደጋጋሚ የተነገረላት የነገ የተስፋይቱን ምድር  💚💛❤ኢትዮጵያን💚💛❤ አሳያቸዋለሁ እሷን እላቸዋለሁ 👌

    ቅሉ እኔ በመልሱ ውስጥ ያለችው  ምድር ዛሬ በዘረኝነት ትብታብ ታስራ በዘረኞች ክፋት ብትናጥም የዛሬ ጭንቋና  ምጧ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ለመውለድ እንደሆንስ ማን ያውቃል!  እኔም  አምናለሁ የዶክተር ወዳጄ ነህ ማህረነን ውብ ሀሳብ ልዋስና አዎን ከአሁኑ ጭንቅና ጥብ በኋላ የከበባት ሀዘን ይሸሻል ያደፈው የድህነት ካባዋ ወልቆ በፍቅር በአንድነት ፀዐዳ የክብር ካባ ይቀየራል እንቆቅልሾቿም በሙሉ ተፈተው  እምዬ ኢትዮጵያ  *የአፍሪካ አልማዝ* ሆና የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም !😍

              👉 ይህ ሀሳብ ከጨለምተኝነት መንገድ የመጣ እንዳልሆነና ይልቁንም   አሁን  እየሆነ ካለው  እውነት የተቀዳ  እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም  ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋

#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም 

✍#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት

በጊዜ ይታከም

*እኔ እምለዉ ይህ ነገር ከበዐሉ ጋር የሚያገናኘዉ ነገር አለ ወይ ወይስ ??????  #ምናልባታዊ_ጥያቄ

*የሠላም የመልካም ምኞት የምስጋናና  የፍቅር በዐል በእንዲህ  መልኩ ነው እንዴ መታጀብ ያለበት???? #ጥያቄው_ከስር_በምስሉላይ_ያሉትንና_መሰሎቻቸው_ብቻ_

 *የጋሽ ጠባቡ የሜንጫ እቅድስ ወደ ተግባር የሚስገባትት ቅድመ እይታስ ይሆን ይሆንን ???? #ስጋት_ለበስ_ጥያቄ_ነው

       አልያማ ቄጤማና አባባ ይዘው ባማረ የባህል አልባሳት ተውበው ከሚያከብሩት ሠላማዊ  ወገኖችና አቋምና ከደመቀዉ የበዐሉ አላማና ጋር የነኚ ምስሉ ላይ የምትመለከቱዋቸዉ አካላት ተግባር ፈፅሞ አይገናኝም 
      ወገኔ  በመሠረቱ ይህ ነገር  ተላላፊ በሽታ ነው ሊያውም   ከአቶ ጠባቡ ወደ መንጋ ጥጋቡ የተዋረሰ በሽታ   የችግሩ ስር ለይቶ የዚህ ተቆጪ አልባ ትውልድ  የክፋት ልምምድ ከአሁኑ ካልታከመ ነጋችን ምን ሊሆን እንደሚችል መሳል  የሚክብድ  አይመስለኝም 
ታዲያ ወገኔ  ይህን ተግባር አይተህ ካላወገዝክ ወይም ምንም  ካልመሰለህ ግን ወዳጄ ይህ የበሽታው የመጀመሪያ ደረጃ ምልክት ነውና ለራስህም ሳይጠናብህ ለኛም ተጨማሪ ጠንቅ ሳትሆንብን እባክህ በጊዜ ታከም !! 

daኒምoni ነኝ ካለሁበት

#በህግ_አምላክ‼

በህግ_አምላክ‼
  
#ጠባቡና_ጥጋቡ
  "የናንተ ክፋት ይበቃናል  እባካችሁ  ነጋችንን አትንጠቁን ተስፋችንን አታጨልሙብን  ህፃናቱን ተውልን"🙏🏽💔 

      የህጻናት አእምሮ የሰጡትን ነው የሚቀበለው  ታዲያ እነዚህን ህጻናት  አዕምሯቸውን ለእውቀትት ሳይሆን ለክፋት ክፍት  እንዲሆን የሚያዘጋጃቸውና በመልካሙ ጎዳና ይመላለሱ ዘንድ እንዳይችሉ መንገዳቸውን በክፋት አጥሮ   ተስፋቸው የሚያጨልመው   ነጋቸውን በፍቅር እንዳይወጥኑ  በግራ ጎኑ የተነሳባቸው  ደብተራቸውን ከእጃቸው  ነጥቆ  ሜንጫ ያስጨበታቸውና የጥላቻ  ፖለቲካ ተዋንያን የክፉ 
አላማ ማራመጃ መሳሪያ ያደረጋቸው  ማነው🤕❓💔     
ይህሥ ሁኔታ  የህፃናቶቹን የነገ ሕይወትና የሀገሪቱን መፃዒ ተስፋስ ምን አይነት መሰረር ሊያሲዘው ይችላል ?  አይ አለመታደል🤕😢 💔 
      መልካም እሴቶቻችንን በአስቀያሚና አስከፊ  ነገሮች እየተካን ብዙ በጎ ነገሮቻችንን ንደን ራሳችን ለራሳችን መሰናክልን እያበጀን ስንጠላለፍ የአንዱ መውደቅ ለሌላው ትንሳአኤ ላይሆን ማሰብ ተስኖን እንዲያው በእውር ድንብር ስንጓዝ  ክፉኛ መስመር እያለፍን ነው አሁን ላይም ቢሆን ቆም ብለን ካላስተዋልን ነጋችን በምን ሊደመደም እንድሚችል መገመት ከባድ አይመስለኝም  🥺⁉

        ወገኔ   እስቲ ዛሬችንን በፍቅር  አኩሪ ስራ ሰርተን  ለተተኪው ትውልድ  መልካም አርዐያ ለመሆን ባያድለን  መጠላለፍና መከፋፋትን እንደ  ባህል ይዘን  መቆሽሻችን ሳያንሰን ዳግም ይባስ ብለን አልፈን ተርፈን ለነገው ትውልድ ጥፋታችንን ለማውረስ መትጋታችን ምን ይባላል ?  አይ አለመታደላችን😢💔   
   ደግ ድጉን ትተን ክፋትን ማዛመት ማዘውተራችን      የዘረኝነትን የጠባብነትንና የጥጋብን ታሪክን ለማቀበል መትጋታችን እኮ ነው አለመታደል🤕😢 
  ማሰብ እየቻልን  ማሰብ ተስኖን ከማስተዋል ወለል ወርደን ከሠፊው ምድር ላይ ጎጥ ለይተን የኛ ሀገር ሳይሆን የኔ መንደር  እያሉ መከፋፈል እኮ ነው አለመታደል 🤕😢 
ተሻሽለን የተሻለች አንዲት ሀገርን ከመገንባት  ይልቅ በዘር ተከፋፍሎ  በድህንት ተደላድሎ መኖርን መምረጥ እኮ ነው  አለመታደል    💔

#ለጋሼ_ከሰማኝ_እጮሀለሁ

 #መንግስት_ሆይ_ወዴት_አለህ 🤕🥺⁉

ውድ መንግስት ሆይ የትላልቆቹ እብደት ሳያንሰን የነ ብጥብጥ   ሱሴ ሽብር እየናጠን  እንደገና  ያም አልበቃ  ብሏቸው የነሱን እብደት ለትውልዱ ሲያዋርሱ  እያየህ ዝም ማለትህ ግን ለምን ነው❓ወይስ  የነዚህ ህፃናት በክፉ መንገድ  መቀረፅና የነገ ማነታቸው  በአንዳንድ    በአልባሌ ፍጡራን አለ አግባብ መመረዝ  ጉዳይ አያሳስብህም ማለት ነው  ❓
 
         ጋሽ መንግስትዬ  ህዝብህ እኮ በወረርሽኙ ምክንያት   የህግና ስነ ስርዐት ትርጉም ጠፍቶበታል የመከባበር የመተሳሰብና አንድ የመሆን ጥቅሙን ዘንግቶታል በቃ ምን አለፋህ  በዘረኝነት ደዌ ክፉኛ ተመቶ  ስርዐት አልበኝነት ፀንቶበት ታሞ የፍቅርና የአንድነት ሀኪም አጥቶ ጣር ይዞታል 🤕🥺
          እናማ ዶክተርዬ ህዝብህን ትፈውሰው ዘንድ መፍትሄው በስርህ ካሉት ጠባብነት እና ጥጋብ የተፀናወታቸውን  ባለ ስልጣን ተብዬ ሊቀ-በሽተኞችህን🤕  መርጠህ በፍቅርና በአንድነትን መንፈስ አጥምቀህ ፈውስና በኢትዮጵያዊነት የክብር ማዕረግ አስመርቅህ ወደ ህዝብህ አሰማራ ምክንያቱም የአንድ እረኛ ጥበብ ለሚጠብቃቸው በጎች ዋስትና እንደሆነ ሁሉ  ላንተም የሹሞችህ መፈወስ ለህዝብህ መዳንና መፈወስ ምንጭ ነውና 🙏🏽
            
#በመጨረሻም

የነ ጠባቡና ጥጋቡ አካሄድ ዛሬ ላይ  እያሳጣን  ያለው የሠላምና አብሮ የመኖር ባህል ሀይ ካልተባለና በዚሁ  ከቀጠለ ለነገ የሚተርፍ ጦሱን  ግዜ  አይፈታውምና ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ በህግ አምላክ  ህግን አክብርረህ አስከብርልን እላለሁ 🙏🏽  አበቃሁ

#daኒሞoni ነኝ ካለሁበት

#እንቆቅልሽ ?

ሀገሩ ማለት ለሀገሬው  ከምንምና ከማንም የምትበልጥበት እስትንፋሱ የልቡ ትርታው የነበረችና  ስለ እርሷ ቢጎዳ እንኳን ጉዳቱን    ከጥቅሙ ይቆጥረው የነበር  ለእርሷ ያለውን  የፍቅሩን ወሰን በቃላት መገደብ የማይቻለው  ከሰንደቋ ስር  ዝቅ ብሎ አንብቶ እንኳን  ስሜቱ የማይረጋለት ከመጀመሪያዋ የሰው መገኛ የትውልድ ምድር የፈለቀ  በጀግንነትና ማሸነፍ ልምዱ ሆኖ  ግዞትን ከነውር ቆጥሮ  ደሙን አፍሶ እጥንቱን ከስክሶ ለነጭ ወራሪ እጁነን ያልሰጠና  በሞቱ የነፃነት ህይወትን ለትውልድ ያወረሰ ጀግና ህዝብ ደግነቱ  ባህሉ ሆኖ  በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ ኩሩ አንድ ህዝብ  የነበሯት ቅድስት ሀገር 🙏🏽

#ዛሬ_ላይ 
👇
  ፍትህ ርቋት በራሷ ህዝቦች ቅኝ ተገዝታ በጉልበትና በትዕቢት የተረኝነት መንፈስ  በጥበብ ሳይሆን በጥጋብ በእውቀት ሳይሆን  በጥበት  በፍቅር ሳይሆን በጉልበት ለእድገት ሳይሆን ለውድቀት   በመንጋ እየታመሰች  በአዋቂ ሳይሆን በታዋቂ እየተመራች ልክ እንደ የህፃናት የእቃቃ ድርድር ተቆጥራ ተጫውተው ሲያብቁም  እንደሚያፈርሱት የጭቃ አሻንጉሊት መስላ የምታያቸው በእድሜና በቁመት እንጂ አዕምሮአቸው የማያድግ እንጭጭ ክሹፉ ፍጡራን ሰልጥነውባት የሚያንገላቷት ምስኪን አገር ማን ትባላለች ❓
                     ሀብታም  ሆና ሳለ ቅሉ ግን ድሀ ህዝቦቿ ከድህንታቸው ጋር ላላቸው ጥልቅ ፍቅርና ቁርኝት  ታምነው ስንፍናቸውን ባለፈ የታሪክ ገድል ሸፍነው ሲያሞካሹ የሚኖሩና እንዲያም ሲል የቂም በቀል  ታሪክን እየተዋረሱ  እርስ በርስ በመባላት ህልሟን ሁሉ በቅዠት የታጨቀ የሚያረጉላት እንጭጭ ፍጡራን ባለቤት  አልባ ሀገር ማን ትባላለች❓

   የዛሬቸውን መባላትቸውንና መከፋፋታቸውን ለትውልድ እንደ በጎ ውርስ ለማስተላለፍ ሌት ተቀን ሲታትሩ  የማይደክማቸው ጉደኛ ፍጡራን ባለቤት የሆነች ምስኪን ሀገር ማን ትባላለች❓

 በስሟ ተጠርተው በከበረ አርማዋ ተለይተው ማንታቸው ከርሳው ማንነት እየተቀዳ በማዕረግ የክብርን ካባ ይለብሱት ዘንድ ያልታደሉ ፍጡሯን ያሏት ምስኪን ሀገር ማን ትባላለች❓

እንደ   አንድ በደም ተሳስሮና ተዋህዶ ክቡር ማንነትን  እንደገነባ ክቡር ህዝብ ተከባብሮ ተፋቅሮ መኖር አቅቶት  በሀገር ከፍታ ተልቆና  አተልቆ መኖርና ማሰብ ተስኖት  ቁልቁል እያሰበ የቁልቁል  ወርዶና ራሱን  አዋርዶ የሚኖር    በመንደር እያሰበ ለክልል የሚዋደቅ  በቅርብ ካለው መልካም ይልቅ በሩቅ ያለን ክፉት አቅርቦ እየሰራ  ባለፈ ታሪክ ከእውነቱም  ከውሸቱም ትርክት እየቀዳ  የቂምን ውርስ ብቻ ተቀብሎ   ዛሬውን ማበላሸቱ ሳያንሰው ለትውልድ የደም መላሽነትን መንፈስ ሊያጋባ የሚተጋ ተቆጪ አልባ ፍጡር ባለቤት ሀገር ማን ናት❓

በፊት ድሮ እኮ አስተዋይ የሀይማኖት አባቶች የሚመሩት ቅን ህዝብ የነበረ ዳሩ ግን ዛሬ ሀይማኖትና ፖለቲካ የተቀላቀሉበት የመንደር ፖለቲከኛ ቄስና ሼክ የሚነዱት በግ የሆነ ህዝብ ባለቤት  የሆነች የጉድ ምድር ማን ትባላለች❓

        ፍቺውን ሁሉም ሰው ሊመልሰው እንደሚችል ባስብም ለምናልባት ግን  ለማያውቋት ግን ሀገር ስጡኝ ብዬ በሰጡኝ ምድር ላይ መልሱን ስሰጣቸው👇

    👌 እሷን አግኝቼ ተደስቼ ምን አጥቼ  ተደስቼ እሷ እኮ በሰዐሊያን ምናብ በጥልቀት  የምትሳል  በገጣምያን የቅኔ ጥበብ ተኩላ በውብ ድምፀት የምትቀነቀን አርማዋ በሰማይ የታተመላት በቅዱስሳን መፀሐፍት በተደጋጋሚ የተነገረላት የነገ የተስፋይቱን ምድር 💚💛❤ኢትዮጵያን💚💛❤ አሳያቸዋለሁ እሷን እላቸዋለሁ 👌

  ቅሉ እኔ በመልሱ ውስጥ ያለችው  ምድር ዛሬ በዘረኝነት ትብታብ ታስራ በዘረኞች ብትናጥም የዛሬ ጭንቋና  ምጧ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ለመውለድ እንደሆንስ ማን ያውቃል!  እኔ ግን አምናለሁ የዶክተር ወዳጄ ነህ ማህረነን ውብ ሀሳብ ልዋስና አዎን ከአሁኑ ጭንቅና ጥብ በኋላ እምዬ ኢትዮጵያ  *የአፍሪካ አልማዝ* ሆና የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም !

              👉 ይህ ሀሳብ ከጨለምተኝነት መንገድ የመጣ እንዳልሆነና ይልቁንም   አሁን  እየሆነ ካለው  እውነት የተቀዳ  እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም  ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋

#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም 

✍#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት