ቅዳሜ 26 ኦክቶበር 2019

#እንቆቅልሽ ?

ሀገሩ ማለት ለሀገሬው  ከምንምና ከማንም የምትበልጥበት እስትንፋሱ የልቡ ትርታው የነበረችና  ስለ እርሷ ቢጎዳ እንኳን ጉዳቱን    ከጥቅሙ ይቆጥረው የነበር  ለእርሷ ያለውን  የፍቅሩን ወሰን በቃላት መገደብ የማይቻለው  ከሰንደቋ ስር  ዝቅ ብሎ አንብቶ እንኳን  ስሜቱ የማይረጋለት ከመጀመሪያዋ የሰው መገኛ የትውልድ ምድር የፈለቀ  በጀግንነትና ማሸነፍ ልምዱ ሆኖ  ግዞትን ከነውር ቆጥሮ  ደሙን አፍሶ እጥንቱን ከስክሶ ለነጭ ወራሪ እጁነን ያልሰጠና  በሞቱ የነፃነት ህይወትን ለትውልድ ያወረሰ ጀግና ህዝብ ደግነቱ  ባህሉ ሆኖ  በእንግዳ ተቀባይነቱ የሚታወቅ ኩሩ አንድ ህዝብ  የነበሯት ቅድስት ሀገር 🙏🏽

#ዛሬ_ላይ 
👇
  ፍትህ ርቋት በራሷ ህዝቦች ቅኝ ተገዝታ በጉልበትና በትዕቢት የተረኝነት መንፈስ  በጥበብ ሳይሆን በጥጋብ በእውቀት ሳይሆን  በጥበት  በፍቅር ሳይሆን በጉልበት ለእድገት ሳይሆን ለውድቀት   በመንጋ እየታመሰች  በአዋቂ ሳይሆን በታዋቂ እየተመራች ልክ እንደ የህፃናት የእቃቃ ድርድር ተቆጥራ ተጫውተው ሲያብቁም  እንደሚያፈርሱት የጭቃ አሻንጉሊት መስላ የምታያቸው በእድሜና በቁመት እንጂ አዕምሮአቸው የማያድግ እንጭጭ ክሹፉ ፍጡራን ሰልጥነውባት የሚያንገላቷት ምስኪን አገር ማን ትባላለች ❓
                     ሀብታም  ሆና ሳለ ቅሉ ግን ድሀ ህዝቦቿ ከድህንታቸው ጋር ላላቸው ጥልቅ ፍቅርና ቁርኝት  ታምነው ስንፍናቸውን ባለፈ የታሪክ ገድል ሸፍነው ሲያሞካሹ የሚኖሩና እንዲያም ሲል የቂም በቀል  ታሪክን እየተዋረሱ  እርስ በርስ በመባላት ህልሟን ሁሉ በቅዠት የታጨቀ የሚያረጉላት እንጭጭ ፍጡራን ባለቤት  አልባ ሀገር ማን ትባላለች❓

   የዛሬቸውን መባላትቸውንና መከፋፋታቸውን ለትውልድ እንደ በጎ ውርስ ለማስተላለፍ ሌት ተቀን ሲታትሩ  የማይደክማቸው ጉደኛ ፍጡራን ባለቤት የሆነች ምስኪን ሀገር ማን ትባላለች❓

 በስሟ ተጠርተው በከበረ አርማዋ ተለይተው ማንታቸው ከርሳው ማንነት እየተቀዳ በማዕረግ የክብርን ካባ ይለብሱት ዘንድ ያልታደሉ ፍጡሯን ያሏት ምስኪን ሀገር ማን ትባላለች❓

እንደ   አንድ በደም ተሳስሮና ተዋህዶ ክቡር ማንነትን  እንደገነባ ክቡር ህዝብ ተከባብሮ ተፋቅሮ መኖር አቅቶት  በሀገር ከፍታ ተልቆና  አተልቆ መኖርና ማሰብ ተስኖት  ቁልቁል እያሰበ የቁልቁል  ወርዶና ራሱን  አዋርዶ የሚኖር    በመንደር እያሰበ ለክልል የሚዋደቅ  በቅርብ ካለው መልካም ይልቅ በሩቅ ያለን ክፉት አቅርቦ እየሰራ  ባለፈ ታሪክ ከእውነቱም  ከውሸቱም ትርክት እየቀዳ  የቂምን ውርስ ብቻ ተቀብሎ   ዛሬውን ማበላሸቱ ሳያንሰው ለትውልድ የደም መላሽነትን መንፈስ ሊያጋባ የሚተጋ ተቆጪ አልባ ፍጡር ባለቤት ሀገር ማን ናት❓

በፊት ድሮ እኮ አስተዋይ የሀይማኖት አባቶች የሚመሩት ቅን ህዝብ የነበረ ዳሩ ግን ዛሬ ሀይማኖትና ፖለቲካ የተቀላቀሉበት የመንደር ፖለቲከኛ ቄስና ሼክ የሚነዱት በግ የሆነ ህዝብ ባለቤት  የሆነች የጉድ ምድር ማን ትባላለች❓

        ፍቺውን ሁሉም ሰው ሊመልሰው እንደሚችል ባስብም ለምናልባት ግን  ለማያውቋት ግን ሀገር ስጡኝ ብዬ በሰጡኝ ምድር ላይ መልሱን ስሰጣቸው👇

    👌 እሷን አግኝቼ ተደስቼ ምን አጥቼ  ተደስቼ እሷ እኮ በሰዐሊያን ምናብ በጥልቀት  የምትሳል  በገጣምያን የቅኔ ጥበብ ተኩላ በውብ ድምፀት የምትቀነቀን አርማዋ በሰማይ የታተመላት በቅዱስሳን መፀሐፍት በተደጋጋሚ የተነገረላት የነገ የተስፋይቱን ምድር 💚💛❤ኢትዮጵያን💚💛❤ አሳያቸዋለሁ እሷን እላቸዋለሁ 👌

  ቅሉ እኔ በመልሱ ውስጥ ያለችው  ምድር ዛሬ በዘረኝነት ትብታብ ታስራ በዘረኞች ብትናጥም የዛሬ ጭንቋና  ምጧ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ለመውለድ እንደሆንስ ማን ያውቃል!  እኔ ግን አምናለሁ የዶክተር ወዳጄ ነህ ማህረነን ውብ ሀሳብ ልዋስና አዎን ከአሁኑ ጭንቅና ጥብ በኋላ እምዬ ኢትዮጵያ  *የአፍሪካ አልማዝ* ሆና የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም !

              👉 ይህ ሀሳብ ከጨለምተኝነት መንገድ የመጣ እንዳልሆነና ይልቁንም   አሁን  እየሆነ ካለው  እውነት የተቀዳ  እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም  ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋

#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም 

✍#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ