እሷ እኮ ነው በሰዐሊያን ምናብ በጥልቀት የምትሳል በገጣምያን የቅኔ ጥበብ ተኩላ በውብ ድምፀት የምትቀነቀን አርማዋ በሰማይ የታተመላት በቅዱስሳን መፀሐፍት በተደጋጋሚ የተነገረላት የነገ የተስፋይቱን ምድር 💚💛❤ኢትዮጵያን💚💛❤ አሳያቸዋለሁ እሷን እላቸዋለሁ 👌
ቅሉ እኔ በመልሱ ውስጥ ያለችው ምድር ዛሬ በዘረኝነት ትብታብ ታስራ በዘረኞች ክፋት ብትናጥም የዛሬ ጭንቋና ምጧ የነገ ብሩህ ተስፋዋን ለመውለድ እንደሆንስ ማን ያውቃል! እኔም አምናለሁ የዶክተር ወዳጄ ነህ ማህረነን ውብ ሀሳብ ልዋስና አዎን ከአሁኑ ጭንቅና ጥብ በኋላ የከበባት ሀዘን ይሸሻል ያደፈው የድህነት ካባዋ ወልቆ በፍቅር በአንድነት ፀዐዳ የክብር ካባ ይቀየራል እንቆቅልሾቿም በሙሉ ተፈተው እምዬ ኢትዮጵያ *የአፍሪካ አልማዝ* ሆና የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም !😍
👉 ይህ ሀሳብ ከጨለምተኝነት መንገድ የመጣ እንዳልሆነና ይልቁንም አሁን እየሆነ ካለው እውነት የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም
✍#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ