ቅዳሜ 26 ኦክቶበር 2019

#በህግ_አምላክ‼

በህግ_አምላክ‼
  
#ጠባቡና_ጥጋቡ
  "የናንተ ክፋት ይበቃናል  እባካችሁ  ነጋችንን አትንጠቁን ተስፋችንን አታጨልሙብን  ህፃናቱን ተውልን"🙏🏽💔 

      የህጻናት አእምሮ የሰጡትን ነው የሚቀበለው  ታዲያ እነዚህን ህጻናት  አዕምሯቸውን ለእውቀትት ሳይሆን ለክፋት ክፍት  እንዲሆን የሚያዘጋጃቸውና በመልካሙ ጎዳና ይመላለሱ ዘንድ እንዳይችሉ መንገዳቸውን በክፋት አጥሮ   ተስፋቸው የሚያጨልመው   ነጋቸውን በፍቅር እንዳይወጥኑ  በግራ ጎኑ የተነሳባቸው  ደብተራቸውን ከእጃቸው  ነጥቆ  ሜንጫ ያስጨበታቸውና የጥላቻ  ፖለቲካ ተዋንያን የክፉ 
አላማ ማራመጃ መሳሪያ ያደረጋቸው  ማነው🤕❓💔     
ይህሥ ሁኔታ  የህፃናቶቹን የነገ ሕይወትና የሀገሪቱን መፃዒ ተስፋስ ምን አይነት መሰረር ሊያሲዘው ይችላል ?  አይ አለመታደል🤕😢 💔 
      መልካም እሴቶቻችንን በአስቀያሚና አስከፊ  ነገሮች እየተካን ብዙ በጎ ነገሮቻችንን ንደን ራሳችን ለራሳችን መሰናክልን እያበጀን ስንጠላለፍ የአንዱ መውደቅ ለሌላው ትንሳአኤ ላይሆን ማሰብ ተስኖን እንዲያው በእውር ድንብር ስንጓዝ  ክፉኛ መስመር እያለፍን ነው አሁን ላይም ቢሆን ቆም ብለን ካላስተዋልን ነጋችን በምን ሊደመደም እንድሚችል መገመት ከባድ አይመስለኝም  🥺⁉

        ወገኔ   እስቲ ዛሬችንን በፍቅር  አኩሪ ስራ ሰርተን  ለተተኪው ትውልድ  መልካም አርዐያ ለመሆን ባያድለን  መጠላለፍና መከፋፋትን እንደ  ባህል ይዘን  መቆሽሻችን ሳያንሰን ዳግም ይባስ ብለን አልፈን ተርፈን ለነገው ትውልድ ጥፋታችንን ለማውረስ መትጋታችን ምን ይባላል ?  አይ አለመታደላችን😢💔   
   ደግ ድጉን ትተን ክፋትን ማዛመት ማዘውተራችን      የዘረኝነትን የጠባብነትንና የጥጋብን ታሪክን ለማቀበል መትጋታችን እኮ ነው አለመታደል🤕😢 
  ማሰብ እየቻልን  ማሰብ ተስኖን ከማስተዋል ወለል ወርደን ከሠፊው ምድር ላይ ጎጥ ለይተን የኛ ሀገር ሳይሆን የኔ መንደር  እያሉ መከፋፈል እኮ ነው አለመታደል 🤕😢 
ተሻሽለን የተሻለች አንዲት ሀገርን ከመገንባት  ይልቅ በዘር ተከፋፍሎ  በድህንት ተደላድሎ መኖርን መምረጥ እኮ ነው  አለመታደል    💔

#ለጋሼ_ከሰማኝ_እጮሀለሁ

 #መንግስት_ሆይ_ወዴት_አለህ 🤕🥺⁉

ውድ መንግስት ሆይ የትላልቆቹ እብደት ሳያንሰን የነ ብጥብጥ   ሱሴ ሽብር እየናጠን  እንደገና  ያም አልበቃ  ብሏቸው የነሱን እብደት ለትውልዱ ሲያዋርሱ  እያየህ ዝም ማለትህ ግን ለምን ነው❓ወይስ  የነዚህ ህፃናት በክፉ መንገድ  መቀረፅና የነገ ማነታቸው  በአንዳንድ    በአልባሌ ፍጡራን አለ አግባብ መመረዝ  ጉዳይ አያሳስብህም ማለት ነው  ❓
 
         ጋሽ መንግስትዬ  ህዝብህ እኮ በወረርሽኙ ምክንያት   የህግና ስነ ስርዐት ትርጉም ጠፍቶበታል የመከባበር የመተሳሰብና አንድ የመሆን ጥቅሙን ዘንግቶታል በቃ ምን አለፋህ  በዘረኝነት ደዌ ክፉኛ ተመቶ  ስርዐት አልበኝነት ፀንቶበት ታሞ የፍቅርና የአንድነት ሀኪም አጥቶ ጣር ይዞታል 🤕🥺
          እናማ ዶክተርዬ ህዝብህን ትፈውሰው ዘንድ መፍትሄው በስርህ ካሉት ጠባብነት እና ጥጋብ የተፀናወታቸውን  ባለ ስልጣን ተብዬ ሊቀ-በሽተኞችህን🤕  መርጠህ በፍቅርና በአንድነትን መንፈስ አጥምቀህ ፈውስና በኢትዮጵያዊነት የክብር ማዕረግ አስመርቅህ ወደ ህዝብህ አሰማራ ምክንያቱም የአንድ እረኛ ጥበብ ለሚጠብቃቸው በጎች ዋስትና እንደሆነ ሁሉ  ላንተም የሹሞችህ መፈወስ ለህዝብህ መዳንና መፈወስ ምንጭ ነውና 🙏🏽
            
#በመጨረሻም

የነ ጠባቡና ጥጋቡ አካሄድ ዛሬ ላይ  እያሳጣን  ያለው የሠላምና አብሮ የመኖር ባህል ሀይ ካልተባለና በዚሁ  ከቀጠለ ለነገ የሚተርፍ ጦሱን  ግዜ  አይፈታውምና ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ በህግ አምላክ  ህግን አክብርረህ አስከብርልን እላለሁ 🙏🏽  አበቃሁ

#daኒሞoni ነኝ ካለሁበት

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ