ይሄዉልህ ወዳጄ በዚች ምድር የመገኘታችን ምሥጢር የሆነዉ ፈጣሪም ቢሆን ሲፈጥረን ከሌሎች እንስሳት ለይቶ ክፉና ደግ ብለን የምንለይበትን አዕምሮ ፈጥሮ ክቡር ሠዉ አድርጎ የከወነን በማሥተዋልና በፍቅር እንኖር ዘንድ ነበር 🥺
ዳሩ ምን ያረጋል እንደሠዉ ተፈጥረን ሠዉኛ ባህሪያችንን በማይሆን ጭካኔ ለዉጠን እንደ አራዊት መኖርን መረጥን እንጂ ያሳዝናል አይደል ወዳጄ🥺
ምን መሠለህ ወዳጄ ማንም ሁን ምንም ሁን የየትኛዉም እምነት ተከታይ ወይም የየትኛዉም አሥተሳሰብ አራማጅ ሁን የማይካደዉ ነጥብ ግን ሁላችንንም የፈጠረን አንድ አካል አለ እርሡ ደሞ ፍቅር ነዉ ። እንዲያ ከሆነ ደሞ ለኛ ከፍቅር በላይ ሊገዛን የሚችል አንዳችም ነገር አይኖርም ።
ወዳጄ ፍቅርን ከተለያዩ ነገሮች ጋር አያይዘን ልንገልፀዉ እንችላለን ዳሩ ግን አንዱንም አይነት ፍቅር ከአሉታዊ ነገረ ጋር ልናነፃፅረዉ አይቻለንም ምክንያቱም መልካም ነገርን በመልካም ካልሆነ በሌላ መንገድ ለመግለፅ የክፉ ነገር ደቀመዝሙር መሆንን ይጠይቃልና እንዲያ ከሆነ ደሞ የክፋትና የጥላቻ ምንጩም ፈጣሪዉም ሠይጣን ነዉ ሥለዚህ ከየትኛዉ ጎራ እንደምትመደብ መልሡን ላንተዉ እተወዋለሁ ።
ጎራህ ሥትለይም ደሞ ወዳጄ 🤔
በአሁኑ ሠዐት ከጊዜ ወደጊዜ መልኩን እየቀያየረና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ አንዳንድ አካላት መጥፎ የጎጠኝነት ሥሜትን ቼ ብለዉ በዉር ድንብር የዘረኝነት ፈረሥ መድረሻቸዉን ሳያሥተዉሉት በጭፍን ሲጋልቡ ታዲያ አንተም ከነሡም አንዱ ሆነህ በምትዉለዉ ክፋትና በምትከዉነዉ ጥፋት ዉሥጥ ካሥተዋልክ ዛሬ በዘሩ ወይም በሀይማኖቱ ምክንያት የምገድለዉ ሠዉ
*እርሡም እንዳንተ ነገ ህልም እንዳለዉ አትዘንጋ❓
*እርሡም እንዳንተ ተምሮ መለወጥ ሀብት ንብረት ማፍራት ሲልም ያለገደብ ደሥተኛ ህይወትን መኖር እንደሚሻም አትርሳ❓
*እርሡም እንዳንተ ነፃነቱን እንደሚወድም አሥታዉሥ❓
*እንዲያም ሲል እርሡም እንዳንተ ለደቂቃ እግሩ ከቤት ቢወጣ እሥኪመለሥ የማያምኑ እናትና አባት በጉጉት የሚጠብቁ ሚሥትና ልጆች እንዳሉትም እወቅ ❓
♦️ታዲያ ለምን ወዳጄ
ለምን ላልተጨበጠ ተሥፋስ ወንድምህን ትገላለህ❓ እንደምንስ ለነገ ጧሪ ደጋፊዬ ብለዉ በፍቅር ያሳደጉትን እነዚያን ድሀ ወላጆች ወልደዉ መካን ታረጋቸዋለህ❓
ሥለምንሥ የነገ ተሥፋ ህፃናትን ያለ አሳዳጊ ታሥቀራቸዋለህ ህልማቸዉን ለምን ታመክናለህ ሥለምን እኮ ሥለምን ?❓
👆🏼👇🏼የማጠቃለያ መጀመሪያ
የኛነታችን መገለጫ የሆነዉን መከባበራችንን መደጋገፋችንን እንዲሁም አንድነታችንን ሊሸረሽር
በሚችለዉ የዚህ አይነቱ ቀፋፊ የዘረኝነት ድርጊት ተሳታፊዎች ወይ ተዋናዮች አንዴ አይናቸዉ በክፋት ቢታወርም ቅሉ እኛ ግን መልካሙን መንገድ የምንመርጠዉ አካላት በፍቅር ወዴት ነዉ ነገሩ❓
አላማቸሁ ምንድን ነዉ❓ የያዛችሁትሥ መንገድ የት ያደርሳችኃል❓ ልንለቸዉ ይገባል ።
እንደ ጠቅላይ ሚንሥትሩ አገላለፅ " መግደል መሸነፍ መሆኑን " ልናሳዉቃቸዉ ይገባል።
አልያ ግን ዘር ቆጥረን እኛም አብረን ከነሡ ካበርን የዚች አገር የወደፊት እጣ ፈንታ በልዩነት በአለመሥማማት ብቻ ይፈታና አንድነታችን ይጠፋል ይህ ከሆነ ደግሞ ከሆነ ነጋችንን መሳል ከባድ አይሆንም "አደጋ አለዉ"
ሳጠቃልል🔚
እንደ ባህሪያችን ሠዉ እንሁን ወንድምን በመግደል ከሚመጣ ነፃነት ባርነት በሥንት ጣዕሙ እናም
የሀሠት ጠላት የሀቅ ሙላት የሆነዉን ሠላም ከነፃነት ጋር ተዋጅቶና ( ተቀላቅሎ ) ፍትህ ለናፈቋት ሁሉ ብርሀን ሆና ትገለፅላቸዉ ዘንድ 🙏🏽እንፀልይ🙏🏽እላለሁ
👉 ይህ ሀሳብ ከመወገን ወይ ከማንም ጎን ቆሞ ማንንም ለመዉቀሥ ወይም ለማወደሥ በማሠብ የተሠናዳ እንዳልሆነና ይልቁንም ጊዜን ተንተረሶ ካለው እየሆነ ካለዉ እውነታ የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም "አበቃሁ👋
"ዘራችን ኢትዮጵያዊነት ነዉ
ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር"
@ዳaniሞoni ነኝ ካለሁበት

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ