ቅዳሜ 22 ኦገስት 2020

ደሞ ጥያቄ ነዉ🤪

ያ ሠዉ
የሀገር ልኳ ገብቶት ለለዉጧ ሚተጋዉ
ታሪኳን በደማቅ በአረንጓዴ አሻራ የሚሞሻሽረዉ
ታሪኩን በመልካም ማተሙን ያልተወዉ

አዎን ያ ሠዉ
ህዝብ አለሜን ገዝቶ እንደ እናት ሚወደዉ
ይበጃል ያለዉን እንደ አባት ሚመክረዉ
ዛሬን ሳይሆን ነገን በብርሀን ሞልቶ ተግብሮ እያሳየዉ
ህዝቤን በአንድነት በፍቅር እያሠረዉ
በብልፅግና ወግ በቀናዉ ጎዳና በተሥፋ የደመረዉ

ያ ሠዉ
ድካሞቹ ሞልተዉ ፍሬን እያፈሩ ማየቱ ሳያንሠዉ
ከጥበብ ምንጭ ጠልቆ መቀኘት ያሠኘዉ
ንገረኝ ወዳጄ
ምን ነገር አገኘዉ ምን ወጠነ ይህ ሠዉ
ምን አሥቦ ይሆን አጀንዳን በግጥም የሚያከፋፍለዉ

@ዳ@niሞoni

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ