ረቡዕ 4 ኖቬምበር 2020

#እባካችሁ

እባካችሁ

አረ ምን አይነት በሽታ ነዉ  ግን የተቆራኘን   ወገኔ እንዴ በዚህ ክፉ ቀን እርሥ በርሥ ተከፋፍለን እየከፋፋን መጋደላችን ሳይበቃን እንደገና እንደመልካም ነገር  በህይወት የተለዩ ወገኖችን ምሥል በማህበራዊ ሚዲያ እየለቀቅን የምንሳለቀዉ ነገር አረ ምንድን ነዉ ?

     አረ በፈጣሪ ጭካኔያችን በልክ ይሁን ባያድለን እነጂ እኮ ሟችም ገዳይም ጦርን የሚሠብቁት ለጠላት  እንጂ እርሥ በርሥ ባልነበር ዳሩ ምን ይሆናል የቀን ጎዶሎ ለፖለቲካ ቁማር እንዲመች በመሀከላቸዉ ቅራኔን ፈጥረዉ እርሥ በርሥ እንጢጠፋፉ አዘጋጇቸዉ ተጋደሉ 

     ወገኔ በዚህ መከፋፋት አትራፊ የለም አሸናፊ ተሸናፊም የለም ዛሬ ትርፍ ለሌለዉ መሥዋዕትነት ህይወቱን ያጣዉ ወታደር እኮ እንዳተዉ ምሥኪን ደሀ እናትና አባት አሉት እንደዘበት እንደቀልድ ፖሥት የምታረገዉ የአሥክሬን ፎቶ ልታሥበዉ  ከምትችለዉ በላይ ከባድ ጥፋትን ያሥከትላል 

እባካችሁ እባካችሁ ዘግናኝ  ምሥሎችን አትልቀቁ

@dኒmoኒ

በፖለቲካ

"በፖለቲካ ውሰጥ ምንም ነገር በድንገት አይፈጠርም፣ 
ድንገተኛ ነገር እንኳ ቢፈጠር፣ ነገሩ ድንገተኛ እንዲመስል ተደርጎ #ስለመታቀዱ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ።" 
          - ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት

https://www.facebook.com/179943078867733/posts/1405744026287626/

#የትግራዋይ_እናት

እኔ ግን የትግራይ እናት ታሳዝነኛለች እድሜ ልኳን ልጆቿን በጦርነት እንደተነጠቀች እንደገበረች 
     ጥቂት አካላት የፖለቲካ ስልጣን ወንበራቸዉን አንቀዉ ሲቆምሩ   የምሥኪን እናት  ልጆችን እርስ በርስ  ያዋጓቸዋል እርሥ በርሥ   ያጨካክኗክኗቸዋል ወንድም ወንድሙን ገሎ ጀግና ላይባል ለናቱ የዘላለም ሀዘንን ከማዉረሥና ለራሡም ፀፀት ከማቆየት በቀር ትርፍ የለዉም 
ሀዘናችን በዛ ፈጣሪ በቃችሁ ይበለን 😭

@ዳaniሞoni

ዓርብ 25 ሴፕቴምበር 2020

ዛሬ ወይም መቼም

ወዳጄ ሁሉም ሠዉ አንድ አይደለም በዚህች ኮንትራት አለም እንደ መልካችን ባህሪያችንም ይለያያል ያለለት ለመልካምነትና ለበጎ ስራ ተለይቶ በምድር ሠላሙን በሠማይ ደሞ የዘለዐለም ቤቱን ይሠራል ያላለለት ደሞ ከሁለት አጥ ሆኖ የፀፀትን ማቅ ይለብሳል ዳሩ በሠማይ ፀፀት የለም እንጂ ☺️
ታዲያ ምንግዜም ገጣሚዉ እንዳሉት 
          ፅድቅና ኩነኔ ቢኖሩም ባይኖሩም
           ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም
መልካም ነገር ሠርተን ደሥተኛ ህይወትን እንኑር 

ቅዳሜ 22 ኦገስት 2020

ደሞ ጥያቄ ነዉ🤪

ያ ሠዉ
የሀገር ልኳ ገብቶት ለለዉጧ ሚተጋዉ
ታሪኳን በደማቅ በአረንጓዴ አሻራ የሚሞሻሽረዉ
ታሪኩን በመልካም ማተሙን ያልተወዉ

አዎን ያ ሠዉ
ህዝብ አለሜን ገዝቶ እንደ እናት ሚወደዉ
ይበጃል ያለዉን እንደ አባት ሚመክረዉ
ዛሬን ሳይሆን ነገን በብርሀን ሞልቶ ተግብሮ እያሳየዉ
ህዝቤን በአንድነት በፍቅር እያሠረዉ
በብልፅግና ወግ በቀናዉ ጎዳና በተሥፋ የደመረዉ

ያ ሠዉ
ድካሞቹ ሞልተዉ ፍሬን እያፈሩ ማየቱ ሳያንሠዉ
ከጥበብ ምንጭ ጠልቆ መቀኘት ያሠኘዉ
ንገረኝ ወዳጄ
ምን ነገር አገኘዉ ምን ወጠነ ይህ ሠዉ
ምን አሥቦ ይሆን አጀንዳን በግጥም የሚያከፋፍለዉ

@ዳ@niሞoni

እሑድ 2 ኦገስት 2020

#Ethiopia

🇪🇹🇪🇹What a joy and a good feeling to hear and see the good news about our country, 

#itsmydam
#OurvoiceforOurDam  #itsmydam


#itsmydam 
#OurvoiceforOurDam  
#itsmydam

ስለአገራችን መልካም ዜና እንደመስማትና እንደማየት ምን ደሥታን የሚሠጥና ጥሩ ስሜት  የሚያጭር ነገር አለ  አቦ ወዳጄ ፈጣሪ ይህችን ዞሮ መግቢያ እናታችንን ሀገራችንን ሠላሟን መልሶ መልኬም መልካሟን ብቻ ያሠማን ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን ይጠብቅልን 

ቅዳሜ 1 ኦገስት 2020

አሥተዉል

በመፅናት መጓዝ ድልድይ ነው
ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ግርግዳ ነው

በፍቅር እንኑር

ወዳጄ በዚች የኮንትራት አለም የሚፈፀም ማንኛዉም ነገር ሁሉ ትክክል የሚሆነዉ በፍቅርና በፍቅር ሲደረግ ብቻ ነዉ ❕
ይሄዉልህ ወዳጄ በዚች ምድር የመገኘታችን ምሥጢር የሆነዉ ፈጣሪም ቢሆን ሲፈጥረን ከሌሎች እንስሳት ለይቶ ክፉና ደግ ብለን የምንለይበትን አዕምሮ ፈጥሮ ክቡር ሠዉ አድርጎ የከወነን በማሥተዋልና በፍቅር እንኖር ዘንድ ነበር 🥺
ዳሩ ምን ያረጋል እንደሠዉ ተፈጥረን ሠዉኛ ባህሪያችንን በማይሆን ጭካኔ ለዉጠን እንደ አራዊት መኖርን መረጥን እንጂ ያሳዝናል አይደል ወዳጄ🥺

ምን መሠለህ ወዳጄ ማንም ሁን ምንም ሁን የየትኛዉም እምነት ተከታይ ወይም የየትኛዉም አሥተሳሰብ አራማጅ ሁን የማይካደዉ ነጥብ ግን ሁላችንንም የፈጠረን አንድ አካል አለ እርሡ ደሞ ፍቅር ነዉ ። እንዲያ ከሆነ ደሞ ለኛ ከፍቅር በላይ ሊገዛን የሚችል አንዳችም ነገር አይኖርም ።

ወዳጄ ፍቅርን ከተለያዩ ነገሮች ጋር አያይዘን ልንገልፀዉ እንችላለን ዳሩ ግን አንዱንም አይነት ፍቅር ከአሉታዊ ነገረ ጋር ልናነፃፅረዉ አይቻለንም ምክንያቱም መልካም ነገርን በመልካም ካልሆነ በሌላ መንገድ ለመግለፅ የክፉ ነገር ደቀመዝሙር መሆንን ይጠይቃልና እንዲያ ከሆነ ደሞ የክፋትና የጥላቻ ምንጩም ፈጣሪዉም ሠይጣን ነዉ ሥለዚህ ከየትኛዉ ጎራ እንደምትመደብ መልሡን ላንተዉ እተወዋለሁ ።

ጎራህ ሥትለይም ደሞ ወዳጄ 🤔

በአሁኑ ሠዐት ከጊዜ ወደጊዜ መልኩን እየቀያየረና ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ አንዳንድ አካላት መጥፎ የጎጠኝነት ሥሜትን ቼ ብለዉ በዉር ድንብር የዘረኝነት ፈረሥ መድረሻቸዉን ሳያሥተዉሉት በጭፍን ሲጋልቡ ታዲያ አንተም ከነሡም አንዱ ሆነህ በምትዉለዉ ክፋትና በምትከዉነዉ ጥፋት ዉሥጥ ካሥተዋልክ ዛሬ በዘሩ ወይም በሀይማኖቱ ምክንያት የምገድለዉ ሠዉ

*እርሡም እንዳንተ ነገ ህልም እንዳለዉ አትዘንጋ❓

*እርሡም እንዳንተ ተምሮ መለወጥ ሀብት ንብረት ማፍራት ሲልም ያለገደብ ደሥተኛ ህይወትን መኖር እንደሚሻም አትርሳ❓

*እርሡም እንዳንተ ነፃነቱን እንደሚወድም አሥታዉሥ❓

*እንዲያም ሲል እርሡም እንዳንተ ለደቂቃ እግሩ ከቤት ቢወጣ እሥኪመለሥ የማያምኑ እናትና አባት በጉጉት የሚጠብቁ ሚሥትና ልጆች እንዳሉትም እወቅ ❓

♦️ታዲያ ለምን ወዳጄ

ለምን ላልተጨበጠ ተሥፋስ ወንድምህን ትገላለህ❓ እንደምንስ ለነገ ጧሪ ደጋፊዬ ብለዉ በፍቅር ያሳደጉትን እነዚያን ድሀ ወላጆች ወልደዉ መካን ታረጋቸዋለህ❓
ሥለምንሥ የነገ ተሥፋ ህፃናትን ያለ አሳዳጊ ታሥቀራቸዋለህ ህልማቸዉን ለምን ታመክናለህ ሥለምን እኮ ሥለምን ?❓

👆🏼👇🏼የማጠቃለያ መጀመሪያ

የኛነታችን መገለጫ የሆነዉን መከባበራችንን መደጋገፋችንን እንዲሁም አንድነታችንን ሊሸረሽር
በሚችለዉ የዚህ አይነቱ ቀፋፊ የዘረኝነት ድርጊት ተሳታፊዎች ወይ ተዋናዮች አንዴ አይናቸዉ በክፋት ቢታወርም ቅሉ  እኛ ግን መልካሙን  መንገድ የምንመርጠዉ አካላት በፍቅር ወዴት ነዉ ነገሩ❓ 
አላማቸሁ ምንድን ነዉ❓ የያዛችሁትሥ መንገድ የት ያደርሳችኃል❓ ልንለቸዉ ይገባል ።
እንደ ጠቅላይ ሚንሥትሩ አገላለፅ " መግደል መሸነፍ መሆኑን " ልናሳዉቃቸዉ ይገባል።
አልያ ግን ዘር ቆጥረን እኛም አብረን ከነሡ ካበርን የዚች አገር የወደፊት እጣ ፈንታ በልዩነት በአለመሥማማት ብቻ ይፈታና አንድነታችን ይጠፋል ይህ ከሆነ ደግሞ ከሆነ ነጋችንን መሳል ከባድ አይሆንም "አደጋ አለዉ"

ሳጠቃልል🔚
እንደ ባህሪያችን ሠዉ እንሁን ወንድምን በመግደል ከሚመጣ ነፃነት ባርነት በሥንት ጣዕሙ እናም
የሀሠት ጠላት የሀቅ ሙላት የሆነዉን ሠላም ከነፃነት ጋር ተዋጅቶና ( ተቀላቅሎ ) ፍትህ ለናፈቋት ሁሉ ብርሀን ሆና ትገለፅላቸዉ ዘንድ 🙏🏽እንፀልይ🙏🏽እላለሁ

👉 ይህ ሀሳብ ከመወገን ወይ ከማንም ጎን ቆሞ ማንንም ለመዉቀሥ ወይም ለማወደሥ በማሠብ የተሠናዳ እንዳልሆነና ይልቁንም ጊዜን ተንተረሶ ካለው እየሆነ ካለዉ እውነታ የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም "አበቃሁ👋

       "ዘራችን ኢትዮጵያዊነት ነዉ
                       ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር"

@ዳaniሞoni ነኝ ካለሁበት 

ሐሙስ 9 ጁላይ 2020

#ብሄራዊ_ጀግና

#የህዳሴዉ_ግድብ_የጀግናዉ_ሀዉልት_ነዉ!!💚💛❤️

የ ህዳሴ ግድቡን ስናስብ መቼም ምርጡን ጀግናችንን የህዳሴዉን አባት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ  አንዘነጋዉም 
 ያ ጀግና ኢንጅነር  እኮ ለሀገሩ  እውቀቱን ጊዜዉን ሲልም ክቡር ህይወቱንም ጭምር የሰጠ ነዉ አንተ ጀግናችን ሆይ ለኛ ብረሀን ማየት አንተ ጠፍተህ ስለዋልክልን ሁሉ እናመሠግናለን የልፋትህ ዉጤትና የተዉክልን አደራ እዉን ሊሆን ቀርቧል አንተም ሁሌም ብሄራዊ ጀግናችን ነህና አንረሳህም በልባችን  ፀንተህ ትኖራለህ
💚💛❤️ ነብስህን ይማረዉ ጀግናዉ ኢንጂነር ስመኘዉ በቀለ💚💛❤️ 🙏

@dኒmoኒ

እሑድ 5 ጁላይ 2020

When people hurt you over and over, think of  them as sandpaper. They may scratch and hurt a bit. but in the end, you end up polished and they end up useless.

እሑድ 10 ሜይ 2020

#ይሄ_ሠዉ_ጀግና_ነዉ

#አንተ_ኢትዮጵያዊ_ነህ

ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ መሠለህ ወዳጄ

* አንዳንድ ሠሞን አንድ ሠዉ "በሚገባዉ" ቦታ ሠዐትና ሁኔታ ላይ ሢወከልና ወዲያዉም በወቅቱ ተፈትኖ የሚመጥን ሆኖ ሲገኝ ሥለገባዉ "አለ" ብለህ ትጠራዋለህ ሥለሚገባዉም "አለልን" ብለህ ትኮራበታለህ ለነገህም በተሥፋ የምጠብቀዉ ሁነኛ ሠዉ እንደሆነ ትናገርለታለህ የኔ ጀግና ሥትልም ትመሠክርለታለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

*የክፋትና የቂም በቀል ታሪኮችን በሚያዋድዱንና አንድ በሚያረጉን ተግባራት እየቀየረ ከትናንት የታሪክ ማህደር ሥንመዝ ለዛሬ መማሪያ ይሆነን ዘንድ እንጂ ለነገ የበቀል መሳሪያ ለማድረግ እንዳልሆነ ተግቶ ሲያስተምር ፍቅርን ሲሰብክ ስታይ የዘረኝነትን ክፋትና ጠንቁ ሥር እንዳይሠድና ዳፋዉ ለትዉልድ እንዳይተርፍ በጥበብ ሲዋጋ ስትመለከት ዛሬ ላይ ነገህን አብርቶ ብሩህ ተሥፋን ሊያሳይህ ሲተጋ ስታይ ንጉሡን ወዳጄ ትገልፀዉ ዘንድ አቅም ያንስህና ሥለ እዉነት በቃ ዝም ትላለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

*በቃ ምን አለፋህ ወዳጄ ሀገርህን ሥሟን በመልካም ሥላወሳ ብቻ ሥሙን በፍቅር ቀለም በልብህ ታትመዋለህ ከመልካም ሥሞች ተርታ ትመድበዋለህ ሥላከበራት ኢትዮጵያ ከአንገት ሰበር ከወገብህ አጠፍ ከጉልበትህ ሸብረክ ብለህ ካከበራት በላይ ታከብረዋለህ ጀግናዬም ትለዋለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

"በቅሎን አባትህ ማነው? ቢሉት ፈረስ አጎቴ ነው" ይላል እንዲሉ ጊዜአችን ያላገናዘቡና በሠነፍ የዘር ፖለቲካ እሳቤያቸዉ አቅላቸዉን የሳቱ የብጥብጥ ሀሳዊ ነብያቶቹ ጠባቡና ጥጋቡ ላይግባቡ ተጋብተዉ የጥላቻ አሥተምህሯቸዉን በ40 መንገድ እየመነዘሩ ትንሽነታቸዉ የማሳነስ ወግ እንዲያወጉ ብታሥገድዳቸዉ ከማይገባቸዉ ጥግ ቆመዉ ትንቢታቸዉ አገር ለማሸበር ህዝብን እስከመቅጠር ሲደርስና የአርግ አታርግ የሁን አትሁንና የአበቃልህ ቀጠሮን ባዘለ ሥካር ናዉዘዉ ሲቅበዘበዙ" ንጉሱ አይቶና ተረድቶ በጊዜ ለኩሉ ጥበብ በማሥተዋል ሲያልፍ ስታይ ወዳጄ ትደመማለህ እኮ ነዉ የምልህ ታዲያ ያኔ ይህን በሳል መሪ የኔ ጀግና ትለዋለህ ምክንያቱም አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ

እናም እኔም እልሀለዉ የዚህን ግሩም መሪ ለሀገርህና ለሀገሬ ያለዉን መልካም ሀሳብ ተረድተህ የራዕዩን የህልሙን ታላቅነት ተገንዝበህ ሥለምትደግፈዉና ከጎኑ በመቆምህ ብቻ የኔ ጀግናዬ ነህ
የዶክተር ወዳጄ ነህ ማህረነን ውብ ሀሳብ ልዋስና አዎን "የአፍሪካ አልማዝ" ሀገሬ ከአሁኑ ጭንቅና ጥብ በኋላ የከበባት ሀዘን ሁሉ ይሸሻል ያደፈው የድህነት ካባዋ ወልቆ በፍቅር በአንድነት ፀዐዳ የክብር ካባ ይቀየራል እንቆቅልሾቿም በሙሉ ተፈተው እምዬ ኢትዮጵያ *የአፍሪካ አልማዝ* ሆና የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም !😍


🔚በመጨረሻም
👉 ይህ ሀሳብ ከመወገን ወይ ከማንም ጎን ቆሞ ማንንም ለመዉቀሥ ወይም ለማወደሥ በማሠብ የተሠናዳ እንዳልሆነና ይልቁንም ጊዜን ተንተረሶ ካለው እየሆነ ካለዉ እውነታ የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋

@ዳaniሞoni ነኝ ካለሁበት

ቅዳሜ 9 ሜይ 2020

#መሥከረም_30


👉🏽ወዳጄ "የፖለቲካ ውይይት ሆነ ድርድር ቢደረግ የሚለው ሃሳብ እንደ ሀሳብ "ጤነኛና ጠቃሚ ጉዳይ ሆኖ የሚታይ መሆን ያለበት ቢሆንም " ዳሩ ግን ማን ከማን ይደራደራል ድርድሩሥ በምን መልኩና እንዴት መሆን አለበት አሁን ላይ ጊዜዉና 😷 ሁኔታዉ አመቺ ነዉ ወይ የሚለዉና ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎችንም አገናዝቦ መሆን ይኖርበታል ።

👉🏽 ግና ከሁሉ በፊት ዋናዉ ጉዳይ ወዳጄ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉም ልደራደር ባዩ ወይም የተደራዳሪዉ አካል "የአዕምሮ ጤንነትም" ከግንዛቤ መግባትም ይኖርበታል‼️🔚 ለምን እንዲ አልክ ብለህ እንደማትጠይቀኝ አሥባለሁ ምክንያቱም  የዚህችን ሀገር አንዳንድ ምሁር ነኝ ባዮች ከምሁራኑ ለመለየት ከባድ በመሆኑና አዕምሮው በእዉቀት የተሞላዉንና በጥበት የጨለለዉን ወይም የጨቀየዉን መለየት ሥለሚያሥፈልግ ነዉ አለበለዛ ግን ሀሳቡም ሆነ ሂሳቡም በመጨረሻ ለፍቶ መና እንዲሉ ለማንም ለምንም በማይበጅ ከንቱ አሉባልታ ይታጨቅና "ያለን እንዳለን ሆኖ" የሠላም መንገድ ዘግቶ ለማይሆን ተጨማሪ መቃቃር በር ከፋች ይሆናል እንዲያም ሲል ወደ ዘላለማዊ ክርክርና ብጥብጥ ካልሆነ በቀር ለህዝቡ የሚፈይደዉ አንዳች ነገር አይኖርም🥺

👉🏽 ቅሉ ግን እኮ ወዳጄ የጥጋቡና ጠባቡ የስሌት እይታ አሁን ላይ ሀገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ በአንፃራዊነት ካለማገናዘቡ አልፎ ለህዝቡ ያላቸዉን የንቀት ጥግና አሥበዉለት ሳይሆን አሥበዉበት የሚጎነጉኑትን ክፋት የሚያሳይ ሆኖ ሥታገኘዉ ትደነግጣለህ 😳

👉🏽 የነ ጥጋቡና ጠባቡ ልካቸዉን ያለማወቅ ክፋቱ ደግሞ ወዳጄ ሀገሪቷን ልክ እንደ ቤታቸዉ ቴሌቪዥንና ህዝቡን እንደ መዝናኛ ቻናል መቁጠራቸዉ ነዉ ብቻ ምን ልበልህ በእጃቸዉ በያዙት ሪሞት ባሻቸዉ ሠዐት የፍቅር ሲላቸዉ የጦርነትን ጣቢያ እየመረጡ እንደፈለጉ የሚቀያይሩትና መሽቶ በነጋ ቁጥር አዉቅልሀለሁ እያሉ ሲያሻቸዉ ድምፁን አፍነዉ🤐 ሳይሾማቸዉ ራሳቸዉን በጠበቃነት ሹመዉ የሚናገሩለት🤗 ሊያዉም ደግሞ ቀድሞ ለተቆራኛቸዉ ያልተገራ የሥልጣን ጥም ማርኪያነትና የአመፅ ቀጠሮን እያስያዙ ለመስዕት በግነት የሚያዘጋጁት አድርገዉ ማሠባቸዉ ነዉ 🧐

ወዳጄ የሆነዉ ሆኖ ግን አሁንም ጠባቡና ጥጋቡ ርዕስ አልባ የጥሪ ካርዳቸዉ ከመበተን አልቦዘኑም ያዉ ሊያደርጉት ያሠቡትና ማን አክብሮ ታዳሚያቸዉ እንደሚሆን ባይታወቅም ማለት ነዉ👉⁉️
እንደኔ እንደኔ ግን ጋሽ ጠባቡን በልክ ሁን ሠከን በል ጥጋቡንም በህግ አምላክ ረጋ በል እያልኩ በማሥተዋል በእዉቀት መጓዝ አርነት ያወጣል እላለሁ

በተረፈ መሥከረም 30🤗 እንገናኝ አበቃሁ🙏🏽

#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት

ቅዳሜ 25 ኤፕሪል 2020

#የሠላም_ሠዉ_ነኝ

#የሠላም_ሠዉ_ነኝ

ከእንግዲ ዋይታ አይሆንም ወንድም ወንድሙን አይገለዉም
ቃየል በአቤል ላይ አይነሳም ሠይፍ በልብሽ ባንቺ አያልፍምገበሬዉ የጁን አይጣ እርሻዉን ዳዋ አይብላበት
የእናት ቤት ሞሠብ አይጉደል ይሙላልን ጠጋብ በ


ሺ እዉነት ቢኖኝ ሺ ምክንያት
አልቆምም ለበደል ለክፋት
ትልቅነት የለም ሠዉ ጥሎ
ያለሠላም ትልቅ ህይወት ጎሎ
#የሠላም_ሠዉ_ነኝ ከተሠኘዉ ዜማ የተቀነጨበ


🔹ወዳጄ ይህን መልካም ሥራ ባልተገባ መንገድ በመቶርጎም የተጠመድን አንዳንድ አካላት በተቻለን መጠን በቀናነትና በመልካም ጎኑ ለመመልከት ብንሞክር መልካም ይመሥለኛል🙏🏽

🔹የሚገርምህ እኮ ወዳጄ ሲጀመር በጣም ብዙ የጥፋት ሥራን የሚሠሩና ህዝቡን ከገንዘቡ አልፈዉ በህይወቱ እየቆመሩ ያሉ ከንቱ ፍጡራን ሳሉ ይህን የዘማሪት ሶፍያን ሽባባዉ ስለ ሀገርና ሥለወገን ሠላም የሚያወሳ ሠናይ ሥራ ለመተቸት መነሳትና ምን ሥም እንደሚሠጠዉ አላዉቅም❓

🔹ምክንያቱም ከርዕሱ አንስተን እሥከ መልእክቱ ዉሥጥ ድረሥ ጠልቀን ብንመለከት ጊዜያችንን ያገናዘበና ድንቅ የሠላምና የፍቅር ሠባኪ ዜማ እንደሆነ እናያለን 👌🏼😍

🔹ወዳጄ እንደኔ እንደኔ አንድ ሠዉ የሠላም ሠዉ ነኝ ብሎ ሌሎችንም ለሠላም ለማነሳሳት ሲጥር ሀሳቡ ከክፋት እሥካልሆነ ድረስ ብንችል ማገዝ መርዳት እና አብሮነትን ማሳየት አልያም ለዚያ ካልታደልን ደግሞ በተቃራኒዉ በመጮህ እራሥን ትዝብት ዉሥጥ ከመክተት ዝም ማለቱ ይሻላል ባይ ነኝ ምክንያቱም ስለሠዉ ልጅ ሠላም መሥበክ ሊያሥመሠግን እንጂ እንደ የሠላም ጠላት እንደመሆን ሊያሥወቅሥም ሥለማይችል ሚናችንን እንለይ🧐

🔹ሥለ ሠላም ሥናይ አይናችን ሊቀላ ሥለ ፍቅር ሥንሠማ ጆሮአችን ሊግል ወይ ለመልካም ተብሎ ለተቋጠረ ሥንኝ በተቃራኒዉ ለመተየብ እጃችንን ከተነሳና አንደበታችንን ከጦር ከሠላ እመነኝ ወዳጄ እዛ ጋር ችግር አለ🔴

🔹ወዳጄ በቃ በአጠቃላይ ምን ለማለት ነዉ ለመልካም ነገር አብረን ልንቆም እንጂ ሊያመን የሚገባ አይመሥለኝም
ዳሩ እንደዉም እኮ ክርሥቶስም ህይወቱን የሠጠዉ ለመላዉ የሠዉ ልጅ ፍቅርና ሠላም ያለ ልዩነት መሆኑንም መዘንጋት ያለብን አይመሥለኝም 🙏🏽

🔹ወዳጄ ይልቅ መልካም ፍሬን እናፈራ ዘንድ መልካም ነገርን መዝራት ሥለሚጠበቅብን ብንችል እኛም ያለ ልዩነት የእዉነትና የፍቅርን ሥብከት አጉልተን እንሥበከዉ ለሠላም እየታገልን በሠላም እንኑር ለፍቅር ሥለፍቅር እየኖርን ለሌሎችም አርአያና የፍቅር ሠዉ እንሁን እላለሁ

🔚በመጨረሻም
👉 ይህ ሀሳብ ከመወገን ወይ ከማንም ጎን ቆሞ ማንንም ለመዉቀሥ በማሠብ ከመንገድ የወጣ እንዳልሆነና ይልቁንም አሁን እየሆነ ካለው እውነት የተቀዳ እንደሆን የሚጠፋው የሚኖር ባይጠፋም ማመኑ ግን አይከፋም እላለሁ "አበቃሁ👋

✍#ዳaniሞoni_ነኝ_ካለሁበት

ዓርብ 17 ኤፕሪል 2020

🔴#አደጋ_አለዉ🔴} 🐓 ሳይጮህ_እንንቃ

🔴#አደጋ_አለዉ🔴}

#ወገኔ_ሆይ_የዛሬ_ግድ_የለሽነታችን_ነገ_ላይ_ለሀዘንና_ለመፀፀትና_አሳልፎ_ሳይጠን  🐓 ሳይጮህ_እንንቃ  !!!🔴

 ♦️ወዳጄ ህዝቤ በራሡ በተለያዩ አለማት እየሆነ ካለዉ ከሚታየና ከሚሠማዉ ዜና እንኳን የተማረና ለማሰላሰያ ለመጠንቀቂይ የተሰጠዉን ጊዜዉን እንደ ቀልድ እያባከና መዐት እየጠራ መሆኑን ሥትተዘብ ትደነግጣለህ😨

 ♦️ #😰 ብቻ ግን በሥንቱን ታዝናለህ መሠለህ ወዳጄ ቅሉ ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ ምሥኪኑ ወገኔ ለጥንቃቄ  ያለዉ  መዘናጋትና የተፀናወተዉን ቸልተኝነት ግዴለሽነት ሳይ ነገን እፈራለሁ 😧
  
   ♦️ወዳጄ ዳሩ ግን አሁን ላይ በዚ አደገኛ ጊዜ በዚ ሁኔታና አኳኃን ህዝቡ እንዲንቀሳቀስ  የህዝብ ትራንስፖር መክፈት ሆነ መፍቀድ ትክክል  አይደለም ባይ ነኝ ለዛዉም  በዐልን ተንተረሶ ዘመድን ጥየቃ ለሚል አሳማኝና አንገብጋቤ ላልሆነ ምክንያት ወዳጄ ያለንበት ጊዜ ክፋቱ  እኮ እንኳን ከቤት ወቶ አዉቶቡሥ መናህሪያ ለመሠለፍ ቀርቶ ለወትሮዉ በምዕመኑ ተሞልተዉ ይታዩ የነበሩ 🕌 ⛪የእምነት ተቋማት ዛሬ ላይ   ጭር ብለዉ ከመታየት አድርሷቸዋል አሁንም እላለሁ  የዛሬ ግድየለሽነታችን ነገ ላይ ለሀዘንና ለመፀፀትና አሳልፎ  ሳይጠን  🐓 ሳይጮህ እንንቃ  !!! 🙏🏽
       
    👉  ቅሉ ግን ወዳጄ  🤏🏽"ይሁን እንኳን ቢባል" በቅድሚ  የጤና ጥበቃና  የመንገድ ትራንስፖርት ሚንሥትር በአንድነት በመሆን ተገቢዉን ጥንቃቄ በማረግ ለጉዞ የሚወጣዉን ሠዉ በህግ የታገዘና  አሁን ያለንበትን አስቸጋሪ ጊዜ ባገናዘበ መልኩ እንቅስቃሴ እንዲያረግ የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል እንዲያም ሲል አሥገዳጅ  ሁኔታዎንም  በአግባቡ ለማሥተናበርና  ለማሥተናገድ የሚግዙ አካላትን በማከል መሆን አለበት   ያለበለዚያ የጋሽ መንግስቱ ቸልተኝነት ግን 25  ሚሊየን ተብሎ የተተነበየዉን  ክፉ ዜና የምንሠማመብን ቀን ከማቅረብና አደጋዉን ከማክፋት  የተለየ ትርጉምና  ስም አይሠጠዉም ‼️
 
 #እናም_ሳይቃጠል_🌿  እንዲሉ ጋሼ መንግሥቴ ሆይ ይህ አይነቷ መዘናጋት የምታመጣዉ ጣጣና የምታሥከፍለዉ ዋጋ ከባድ ነዉና ይታሠብበት እላለሁ አበቃሁ 🙏🏽#ፈጣሪ_ምህረቱን_አይንፈገን 🙏🏽

#ዳani_ሞoni_ነኝ_ካለሁበት
🔴
👇🏽                                                         👇🏽

ቅዳሜ 4 ኤፕሪል 2020

#ታዲያ_ምን_ይበጀን❓😭

  #ምን_ይበጀን❓

       ወዳጄ  የሠዉ ልጅ እኮ ሊለካ የማይችል እንዲ እንዲያ  ተብሎ የማይገለፅ የመኖሩን ዋሥትና ሆኖ  ያለ ሀሳብና ያለ ገደብ በነፃና  በነፃነት  እንዲተነፍሥ የተቸረዉን ፀጋ የተሰጠዉን ክቡር  ነገር  በዋጋ የማይተመነዉን ዉድ ገፀበረከት አየር በቀላሉ ዙሪያዉን ከቦት ቢያገኘዉ በገዛ እጁ መርዞ መዉጫ መግቢያ የሚያጣ ምሥኪን ፍጡር ነዉ 😷😭 

           👉 ወዳጄ ያለ ሀሳብ እንዳሻዉ ይምገዉ የነበር አየር ዛሬ  ሥጋቱ ሆኖ 😷 የመኖሩ ምሥጢር የነበረዉን አየር ዛሬ ለመጥፋቱ ምክንያትና እንቆቅልሽ ሲሆንበት  ሥታይ  �ለምን � ካልክ መልሱ የሚሆነዉ አወቅኩ ብሎ ሲራቀቅ  ከፈጣሪዉ ትዕዛዝ ሲያፈነግጥ በገዛ እጁ ነፃነቱን እንዳጣና  ክቡር ሥጦታዉን እራሡ  እንደበከለዉ ሥተረዳ ታዝናለህ 😷😭

     👉ወዳጄ   ያለ ገደብ የተሠጠዉን የህይወቱን ምግብ በከንቱ ሥራዉ አቆሽሾ በገደብ ሢጠቀምና እራሡ የራሡን ነፃነት ለማሠር አለመቦዘኑንና አሥሮም ሢጨነቅ ሥታይ ታዝናለህ 😷😭
  
   👉 👨🏻‍🔬ወዳጄ  አሁን ዛሬ ላይ እኔ ነኝ ያለ ሳይንቲስትና ዶክተር አንተንና እኔን ሊያድነን ይቅርና እራሡን እንኳን ማዳን ተሥኖት የጥፋቱ ሠለባ የመሆኑን ዜና ሥትሠማ ትደነግጣለህ🥺

   🧐👉ወዳጄ በአለም የተከማቸ ሀብት ገንዘብ ንብረትም ሆነ የረቀቀ  ቴክኖሎጂ ችሎ መድሀኒት ሊያሥገኝ አለመቻሉን ሥታይ ትደነግጣለህ😱

#ታድያ_ይበጀን
👇🏽 
     👉አሟልቶ ሠቶን ሠቶን ጎድለን ሥለተገኘን አክብሮ ፈጥሮን ራሳችንን ሥላረከሥን  የሚገባንን ሲሰጠን በማይገባን ሥለተካን የቸርነቱና የምህረቱን ዋጋ ዘንግተን ልካችንን ሥለሳትን አሁን ላይ የሚበጀን ወዳጄ ወደ ፈጣሪ መመለሥና  ሥላረግነዉ ክፉ  እና ሥለሆነብን ሁሉ ዝቅ ብለን ይቅር ይለን ዘንድ መለመንና ነዉ😭🙏🏽

         👉 የመጨረሻ ሳይሆን የመጀመሪያ ምርጫችን መሆን ወደነበረበት ግን በክፋታችን ተጋርደን ወደራቅነዉ መቅረብና  ምህረትን እንለምን በሥተመጨረሻዉ ቢሆን የሚበጀን መድሀኒቱም መፍትሄዉም የሚገኘዉ ከርሡ  ከፈጣሪ እጅ ነዉና ነዉ እርሡ ይቅር ይለን ዘንድ ዝቅ እንበል። አበቃሁ  🙏🏽 ፈጣሪ ምህረቱን  አይንፈገን 🙏🏽

#ዳani_ሞoni_ነኝ_ካለሁበት

ቅዳሜ 28 ማርች 2020

አንኮረኳኮም

የቢላርዚያን መድሐኒት ያገኙት ዶክተር አክሊሉ ለማ ኢትዮጵያዊ ናቸዉ  ! በ4 ኛ ክፍል ትምህርት ተምረነዉ ያለፍነዉን ታሪካቸዉ ዛሬ ላይ 
   የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት አልፏል፡፡"  የሚል መረጃ ስንሰማ ልንደነቅ ሳይሆን
በአገር ልጆች ጥረት ክብር እንጂ ሌላ ለማጣጣል መሯሯጥ ደሥ አይልም please አንኮረኳኮም 

የኢኖቬሽን ሚንስትሩ ዶክተር አብርሃም ለጨለምተኞች ያስተላላፉት መልእክት‪‪

የኢኖቬሽን ሚንስትሩ ዶክተር አብርሃም ለጨለምተኞች ያስተላላፉት መልእክትትላንት ኮረና ቫይረስ አስመልክቶ በኢትዮጵያዉያን ተመመራማሪዎች እየተካሄደ ያለውን ምርምር እና የደረሰበት ደረጃ አስመልክቶ በሰጠነው መግለጫ እንዴት በኢትዮጵያውያን ይህ ሊሆን ይችላል በሚሉ ሃገራቸውን እነሱ የሚያውቁዋትን ያህል እውቀት ብቻ ያላት በሚመስላቸው እና ይህ ስራም ፖሊቲካዊ ገፅታ ሰጥተው እኛ ያላወቅነው እንዴት ይሆናል በሚሉ አካላት ባልሆነ መንገድ ተርጉመው እያቀረቡ  ያሉት ትርክት የለመዱትን የአሉባልታና የውሸት ዜና መስራት መቅረቱን ያልተረዱ እና ሀገራችን ለችግር ግዜ የሚደርሱ አዋቂዎችና ተመራማሪዎች እንዳሉዋት የማያውቁ ወይም ማወቅ የማይፈልጉ ሰዎች ናቸው እና የነሱ ማላዘን ይቀጥላል ሃገራችን እና ህዝቦችዋ ወደ ከፍታ ማማ ይጋዛሉ።  

አሁንም በድጋሚ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ነገር  የተጀመረው የምርምር ስራ እና እስካሁን የተገኘው ውጤት በጣም አበረታች ብቻ ሳይሆን በአጠረ ጊዜ ቀሪ ስራዎች በማጠናቅ ለህዝባችን የጀመረውን የምንጨርስ እና ያልነውን የምናድርግ መሆኑን እንደምናሳይ ነው።  የምርምር ቀሪ ስራዎች ማለትም የአኒማል ቶክሲስቲ እና ክልኒካል ቴስት ስራዎች በተፋጠነ መንገድ እየተሰሩ የሚገኘውን ውጤት ለህዝባችን እንገልፃለን።‬

‪የምርምር ቀሪ ስራዎች የራሳቸው ግዜ የሚወስዱ በመሆናቸው በዚህ መልካም ዜና ምክንያት በፍፁም መዘናጋት አይገባም አያስፈልግም በመንግስት የሚሰጡ የጥንቃቄ እርምጃዎች እንተግብር። ‬

‪ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦችዋን ይባርክ። ‬

#አሳፋሪ_ተግባር



አርብ ሲኒማ ገብቶ ሰኞ ተሰረቀ ተብሎ እንደ ቀልድ የሚወራባት ሀገር ይገርማል😳
  የአንድ ሰዉ የአዕምሮ ንብረት የሆነን ፊልም ለእስክሪን ለማብቃትና ተመልካቹን ለማዝናናት የሚከፈለዉን ጊዜ ገንዘብና እዉቀት ሠርቆ ድካሙን ከንቱ ማስቀረት ትርፉ ምን እንደሆን አላዉቅም ❓

ዳሩ ግን ወዳጆቼ የተሠረቀን ፊልም በማንኛዉም መንገድ 
 ባለመላላክና በተቻለን የሌባ ተባባሪ አለመሆናችንንና ለሙያው ያለንን ክብርና ለሙያተኞቹም ቢሆን   ሲኒማ ገብተን በማየት  የድካማቸዉን ዋጋ እንክፈላቸዉ 🙏🏽

#የ200_ሺ_ጉድጏዱ_ነገርና_ህዝቤ

♦️ #የ200_ሺ_ጉድጏዱ_ነገር_ዉሸትም_ሆነ_እዉነት_ወሬውንለባለቤቱና_ፍርዱንም_ለህግ_ሰዎች_ትተን_ግድ_ካልሆነብን_በቀር_ከቤት_ባለመዉጣት_እራስህንና_ሌሎችን_እጠብቅ🙏🏽

#በጥያቄ_ልጀምርና 🤔ወዳጄ 200 ሺ ጉድጏድ ምናምን እያሉ ወሬ የሚያራቡና የሚያራግቡ የጠባቡና ጥጋቡ ደቀመዛሙርትን ምን ትላቸዋለህ ❓

➖እንደ እኔ ከሆነ ባልተረጋገጠ ወሬ ይህን ምስኪን ህዝብ ከበሽታዉ በላይ ጭንቀት ከምታበዙለት ይልቅ እባካችሁ ብትችሉ አፋችሁን ዝጉ አልያም ልሳናችሁን ለማስተማሪያነት ተጠቀሙበትና እላለሁ፤🙏🏽
➖በዚህ አሥከፊ ሁኔታ ለሌላ ጊዜያዊ ጥቅምም ከሆነ የምትሮጡት ጥቅማችሁ እዉን የሚሆነዉ ህዝቡ ሢኖር ነዉና ቆም ብላችሁ አሥቡ ዛሬን መልካም ነገሮችን በማረግ ተርፋችሁ አትርፉት ከዛም ነገ ላይ እመኑኝ በእርግጠኝነት ታተርፋላችሁ እላለሁ🙏🏽

♦️ዳሩ ግን እኮ ወዳጄ ህዝቤ በራሡ በተለያዩ አለማት እየሆነ ካለዉ ከሚታየና ከሚሠማዉ ዜና እንኳን የተማረና የበሽታውን አሥከፊነት የተረዳዉ አይመሥለኝም 

#ልብ_ብለህ_ከሆነ🔴🧐 
👇🏽                          👇🏽

👉አፉን አፍንጫዉን 😷�በማስክ ሸፍኖ በእጁ ይጨባበጣል🤝🏼🥺

👉በእጁ ማክስ አርጎ ተቃቅፎ ጉንጭ ጉንጭ ይሳሳማል 😳🥺

👉ለጥንቃቄ የሚጠቅሙ ቁሶችን ለመግዛት የተጨናነቀ ሠልፎችን በፋርማሲዎች ትመለከታለህ😳🥺

👉እጅን መታጠብ መልካም ቢሆንም አንድ ላይ እጅብ ብሎ ሲታጠብ ትታዘባለህ😳🥺

👉ለጥንቃቄ ብሎ ባጠለቀዉ ጓንት ምግብን እያነሳ ሲመገብ ሥታይ ትደነግጣለህ😳🥺

👉ዳሩ አንዳንድ ታዋቂ ሠዎችም የተዛባ መረጃን ከመሥጠት አልፈዉ ታጅበዉ እጅ መታጠብን ሲያስተምሩ በሽታዉ በእጅ ብቻ ሳይሆን በትንፋሽ መተላለፋን መዘንጋታቸዉ ያስገርማል😳🥺
☝🏽👉ይህን ስል በሳል በሆነ መንገድ ለወገን ለመድረስ ርቅት በመጠበቅና ንክኪን በመቀነስና ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ እንዴት ከወረርሽኙ እንደምንጠበቅ ግሩም አሥተማሪ መልዕክቶቾችን ከማስተላለፍ አልፈዉ እዉቅናቸዉን ተጠቅመዉ በጉልበታቸዉ በገንዘባቸዉ ሠዎችንም በማስተባበር ለወገን ደራሽነታቸዉን አርዐያነታቸዉን በግልፅ የሚያሳዩንን አያካትትም ለነሡ በክብር እጅ እነሳለሁ🙏🏽

👉ደሞ ይባሥ ብሎ ይህን ሁኔታ ተገን አድርገዉ አላሥፈላጊ ትርፍን ለማጋበስ ከድሀዉ ለመዝረፍ የሚያሠፈሥፉ ነጋዴዎችን የጭካኔያቸዉ ልክ ሥታይ ደሞ ያምሀል😰 ብቻ ግን በሥንቱን ታዝናለህ መሠለህ ወዳጄ ቅሉ ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ ለጥንቃቄ ብሎ ምሥኪን ወገኔ የሚሄድበትን ርቀት ሳይ ነገን እፈራለሁ 😔🥺

እናም ወዳጄ ሳጠቃልልህ የ200 ሺ ጉድጏዱ ነገር ዉሸትም ሆነ እዉነት ወሬውን ለባለቤቱና ፍርዱንም ለህግ ሰዎች ትተን ግድ ካልሆነብን በቀር ከቤት ባለመዉጣት ከወጣንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛንና የእጅ ጓንቶችን በመጠቀም ከሠዎች ጋር ሥንገናኝ ርቀታችንን በመጠበቅ የ በተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች የሚሠጡትን ትምህርቶች ተግባራዊ በማረግ እራሳችንን ጠብቀን ሌላዉንም እንጠብቅ እላለሁ። አበቃሁ 🙏🏽

#ዳani_ሞoni_ነኝ_ካለሁበት