«ልብ ብለው ያንብቡት»
በአንድ ወቅት ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ
በመሀላቸው ልዩ የሆነ ፍቅር ነበራቸው ።
ሁለት ልጆችም ነበራቸው በቤታቸው የሚላስ
የሚቀመስ በመጥፋቱ ይህን ችግር
ለዘለቄታው ለመፍታት ባል ራቅብሎ ሊሰራ
ተሰማምተው ባል ራቅ ወዳለ ከተማ ሄዶ
መስራት ጀመረ። በተከታታይ ለ13 ዓመታት
ሰራ ከዚያ ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድተነሳ
ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ ምን ?ደሞዙ
ምን ሆነ ? በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ
ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው
3000(3 ሺህ) ተሰጠው ምን ያድርግ ?
ተመልሶ እዛው ስራውን ይቀጥል? ወደ
ናፈቁት ቤተሰቦቹ ይሂድ ?ይቻላል ግንተመልሶ
ቢሰራ ደሞዙ መቆራተጡ አይቀሬ ነው ። ወደ
ቤተሰቦቹ እንዳሄድ በ 13 ዓመት ይህን ብቻ
ሰራው ቢልማን ያምነዋል ? ሰለዚህ ሌላ ቦታ
ለመስራት ወሰነ _____ አንድ አባት አገኘ ____
__" ወደዴት ትሄዳለህ ልጄ? ምንስ
ትፈልጋለግህ ?አሉት " እሱም ከመጀመርያው
እስከ መጨረሻው ነገራቸው ።እኒህአባት እንዲ
አሉት እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር
ማግኘት ቀላል ነው"እሱም" እንዴት አባቴ ?
ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም በል አንድ ሺህ
ብሩን አምጣና እነግርሀለሁ አሉት የቸገረው
ነውና ነገሩ እሱም አንስቶ አንድ ሺህ ብሩን
ይሰጣል እኒህ አባትም " አቆራጭ ነው ብለህ
በማታውቀው መንገድ አትሂድ " ይሉታል ።
"ሁለተኛውን ሺህ አምጣና ሁለተኛውን
መንገድ ልንገርህ "ይሉታል እሱም በየዋህነት
ሁለተኛውን ሺህ ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ
"ይሉታል ። "ይኧው ነው አባቴ " ቢላቸው
አዎን ! ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም
አሰፈላጊውና የመጨረሻውን ስጦታዬን
ልስጥህ አሉት ሰጠ። እሳቸውም "ክፉ
ለማድረግ አትቸኩል " ብለው በልልጄ
በቀጥታ ወደ ቤትህ ሂድ ብለው በባዶ ኪሱ ጋር
ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት ።እሱም
ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ።
በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ
መሸ ነጋዴዎቹም ለምን ባቋራጭ አንሄድም
በማለት ጉዞ ጀመሩ እሱም አብሮዋቸው ጉዞ
እንደጀመረ የኛ አባት ምክር ትዝ አለው "
አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ
አትሂድ " የሚለው ሰለዚህ ተመልሶ
በሚያወቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን
ከጨለመ ከተማ ገባ ። "የመሸበት እንግዳ ነኝ
አሳድሩኝ በማለት ጀመረ _______ አንድ ሰው
ተጠግቶ የውልህ ወንድሜ እዛ ስው ቤት ሂድ
ያሳድርሀል ነግር ግን እዛ ስው ቤት የገባ
አይወጣም ለማንኛውም እድልህን ሞክርው
። እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት
የእንግዳ ነው ተብሎ ገባ ። ታድያ ከቤቱ
ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ
ቢነግረው ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴትሆነክ
ተረፍክ ?በል ቢለው ባለ ፀጋው "ከመኑ?" አለ
እንግዳው "ምነውባልከው መስመር ይመጡ
የነበሩ ነጋዴች ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው
ዘረ ከተማው ለቅሶ ብቻ እኮ ነው ።ትዝ አለው
ያቺ በአንድ ሺህ ብር የገዛት ምክር በብር
የማትገዛ እይወቱን አተረፈችለትማለት ነው ።
ሰለ መሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው
ልታቀርብ ከጔዳ ብቅ አለች " ጥያችሁጠፋው
አደል ?" አለች እንግዳው አይኑን ማመን
አልቻለም የተወሰነ አካሉዋ ብቻ ነው ሰው
የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ
እስክትገባ ናፈቀ ። " ከዚህችጋር እንዴት
ትኖራለህ ?" ብሎ እስኪጠይቅ ናፈቀ "ከዚህች
ጋር እንዴት ትኖራለህ ብሎ እስኪጠይቅ ። ወደ
ጓዳ ገባች ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው
የኛ አባት ምክር " በማያገባህ አትግባ "
የሚለው ። ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን
ተቋቁሞ አደረ ። ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ
ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ
ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም
የሞላበት ሜዳ አሳየው እንግዳውም "ይሄ
ምንድ ነው ?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን
በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን ራሱን
እየነቀነቀ ዝም አለ ። የቤቱ ባለቤትም
ተገርሞ በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ
ይህ የምታየው ስው ሁሉ ሰለ ሚስቴ
የማያገባቸውን አሰተያየት ሰለሰጡ የተገደሉ
እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድነት የመጡ ነበሩ
። አንተ ግንታላቅሰ ስለሆንክ የሀብቴን 1/4
ሰጥቼሀለሁና ይዘህ ትሄዳለህተብሎ ባለ ብዙ
ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ ።
እዛች ደሳሳ ጎጆ የደረሰው ከለሊቱ ስድስት
ሰዓት ነበር ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን
አላጣውም በትልቅ እንጨት የምትዘጋ
(የምትደገፍ) በሩን ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች ።
አይኑ ግን ከማያምነው ነገርላይ አረፈ ሚስቱ
ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች ጎንበስ ሲል
ጎራን አየ አነሳ አንገታውን ሊቆርጠው በንዴት
ጦፎ እጁንወደ ላላላላላላላላላላላይይይይ ይይ
አነሳ ______ 3 ተኛው ምክር ትዝ አለው "
ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው ከቤቱ
ውጭ በተጋደመው ዛፍ ላይ ቁጭ አለ
በተቀመጠበት እንክቅፍ ይዞት ሄደ ። ነጋ
ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት
ባሏን አየችው እልልታዋን አቀለጠችው ዘላ
ተጠመጠመችበት ከእንቅልፉ የነቃው ባል
በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ
ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀች """ ይህ
የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ ሁለተኛው ""
ብላ እንግዲህ የመጨረቻው ምክር የልጆቹን
ነፍስ ከማጥፋት እረዳው ማለት ነውሁላችሁም
እስኪ ራሳችኡን ጠይቁ ይህ ሰው ያለዚህ
ምክሮች ቢመጣ ምን ይፈጠር ነበር?
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያድርሡ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ