እሑድ 17 ጃንዋሪ 2016

በር:ፍልስፍና

The Thinker Musee Rodin.jpg

ፈላስፋው
THE THINKER
ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ φιλοσοφία (ፊሎዞፊያ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ፊል መውደድ፣ ሶፊያ ጥበብ ማለት ነው። ሲጋጠም ፍልስፍና ማለት የዕውቀት ፍቅር ማለት ነው።
ጥንታዊ ግሪክ ፍልስፍና ትኩረት አጠቃላይ የሰው ልጅ ዕውቀትን መመርመር ነበር። እንደ ሂሳብ፣ ሳይንስ ያሉ ነጠላ ዕውቀቶች የመጡት ከዚህ አጠቃላይ ዕውቀት ነው። እኒህ ነጠላ ዘርፎች ማጥናት የማይችሏቸውን ሃስቦች ፍልስፍና አሁን ድረስ ያጠናል።
የፍልስፍና ጥናት ዘርፎች

ፍልስፍና

ፍልስፍና በተለያዩ ሰወች የተለያየ ግንዛቤና መረዳት አለው። ሆኖም ከሞላ ጎደል የፍልስፍና ዘርፎችና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንዲህ ይቀርባሉ፡
  • ሜታፊዚክስ : እውንነት ምንድን ነው? እውን የሆነ/የሆኑ ምን ነገሮች አሉ? ከምናስተውለው ዓለም ውጭ ሌላ ዓለም አለ?
  • ሥነ ዕውቀት: አለምን መረዳት እንችላለን? እንዴት ማወቅ እንችላለን? ከራሳችን ውጭ ሌላ ሃሳብ እንዳለ እንዴት እናውቃለን?
  • ሥነ ምግባርሰናይና ዕኩይ (ጥሩና መጥፎ) ልዩነት አላቸው? ካላቸው እንዴት ልንለያቸው እንችላለን? ምን አይነት ምግባር ሰናይ (ጥሩ) ነው? ለአንድ ምግባር ዋጋ ለመስጠት የዋጋ ስርዓት መኖር አለበት፣ ይህ የዋጋ ስርዓት ከየት ይመነጫል? ከአምላክ? ወይስ ከየት? አንድ ምግባር ፍጹም ጥሩ ወይም ፍጹም መጥፎ ሊባል ይችላል? የራበው ሰው ቢሰርቅ ስርቆቱ ዕኩይ ነው? ወይንስ ሥነ ምግባር አንጻራዊ ነው? እንዴት ህይወቴን መምራት አለብኝ? ሁላችንስ እንዴት እንኑር?
  • ሥነ አምክንዮ፡ ትክክለኛ ሃሳብ እንዴት እናመነጫለን? አንድ ሃሳብ ስሜት የማይሰጥ መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የክርክርን አሸናፊ እንዴት መለየት ይቻላል?
  • ሥነ ውበት፡ ኪነት ምንድን ነው? ውበት ምንድን ነው? የውበት ቋሚ መስፈርት አለው? ኪነት መስፈርቱ ነው? እንግዲያስ የውበት ትርጉሙ ምንድን ነው? የኪነት አላማ ምንድን ነው? ኪነት እኛን እንዴት ይነካናል?ኪነት ዕኩይ ሊሆን ይችላል?ኪነት የህብረተሰብን ኑሮ ይሸረሽራል ወይስ ያሻሽላል? አንድ ከዋኝ የሚሰራውን ያውቃል? ለምሳሌድራማ ላይ ፕሬዜዳንት የሆነ ከዋኒ ዕውን ፕሬዜዳንት ሆኖ ሊሰራ ይችላል? የኪነት ተግባር የውኑን አለም መኮረጅ ነው? በመኮረጁ የቱን ያክል ነባራዊውን አለም ያጣምማል?

  

ዕውቅ የምዕራቡ አለም ፈላስፋዎች


ፍልስፍና ካሳለፈው ዘመንና እንዲሁም ከጥናቱ ስፋት የተነሳ ብዙ ጊዜ በአንድ ሃሳብ ላይ የተለያዩ አቋሞች ይንጸባረቃሉ። ስለሆነም ፍልስፍናን በሃሳብ ደረጃ ከማጥናት ይልቅ "የዋና ዋናዎቹ ፈላስፋወች ሃሳብ ምን ነበር?" በማለት ማጥናት ለቀል ይችላል። የሚቀጥሉት ሰዎች ከሞላ ጎደል ዋና ዋናወቹ የምዕራቡ አለም ፈላስፋወች ናቸው። እያንዳንዳቸው ለአሁኑ የምዕራቡ አለም ፍልስፍና ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገው አልፈዋል፦

Kapitolinischer Pythagoras.jpg
Socrates Louvre.jpg
Platon-2.jpg
Aristoteles Louvre.jpg
Seneca.jpg
Augustine of Hippo.jpg
St-thomas-aquinas.jpg
Frans Hals - Portret van René Descartes.jpg
Thomas Hobbes (portrait).jpg
Spinoza.jpg
John Locke.jpg
Gottfried Wilhelm Leibniz.jpg
David Hume.jpg
Immanuel Kant (portrait).jpg
Jeremy Bentham by Henry William Pickersgill detail.jpg
G.W.F. Hegel (by Sichling, after Sebbers).jpg
Schopenhauer.jpg
Kierkegaard.jpg
Karl Marx.jpg
Nietzsche.jpg
Edmund Husserl 1900.jpg
Heidegger 4 (1960) cropped.jpg
Jean-Paul Sartre FP.JPG

የዕለቱ ምርጥ የፍልስፍና ጽሑፍ

ፍልስፍና ማለት እንደኔ ፍልስፍና የገምት ወይም የጥየቄ ኪነ ጥበብ ማለት ነው ። ማለትም የፍልስፍና ውጤት በኅይወታችን ላይ ተግብርነት የለውም...።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ