በሰዓሊ ገብረክርስቶስ ደስታ" ሥነ ሥቅለት"
በተሠኘዉ እዉቅ የሥዕል ጥበብ ሥራ ላይ ተመሥርቶ በድምፃዊ ቴዎድሮሥ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ ) የተፃፈ ምርጥ ግጥም
***ክርስቶስ ወ ገብረክርስቶስ***
እዩት ይሄን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ
በቀይ እየወጋ በደም እየሳላው
እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው
ቀራኒዮ ሆነ የመረጠው ሸራ ጎሎጎታ ሆነ የመረጠው ሸራ
አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ
ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር
ብሩሹን አሹሎት እንደጎኑ ጦር
እየወጋ ሳለው በጣም ጨቀነበት
ገብረክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ
የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ
እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው
ዘሩ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ
መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር
የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው ሀገር
እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር
እንዳንለው ቀይ
በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ
በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው
በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው
ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲማገቱ በቀለሙ ጉዳይ
ሲከራከሩበት
በተመፃዳቂ የምሁራን አንደበት
በአንዱ አፍ ሲጠቁር ባንዱ አፍ ሲነጣ
መታገስ አቃተው ሰዓሊው ተቆጣ
ስሜቱ ገንፍሎ በቡርሽ ጫፍ ወጣ
ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ
ሸራላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ
አልወጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ
ስሎ ስሎ ስሎ ፍቅርን ስሎ ስሎ
በሳለው እየወጋ በደማው እየቀባ
ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀም
እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይሄ አይደለም
እያለ እስኪናገር የስዕሉ አንደበት
ገብረክርስቶስም ለክርስቶስ እሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት
በነጩ ሸራ ላይ እስከአሁን እሚወርድ ደም አፈሰሰበት
ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም
የሁሉ ነው እንጂ የማንም አደለም
ፍቅር ዘር አይደለም ።
በተሠኘዉ እዉቅ የሥዕል ጥበብ ሥራ ላይ ተመሥርቶ በድምፃዊ ቴዎድሮሥ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ ) የተፃፈ ምርጥ ግጥም
***ክርስቶስ ወ ገብረክርስቶስ***
እዩት ይሄን ጠቢብ ሸራው እስኪደማ
በቀይ እየወጋ በደም እየሳላው
እንጨት አመሳቅሎ ዳግም ክርስቶስን ጨርቁ ላይ ሰቀለው
ቀራኒዮ ሆነ የመረጠው ሸራ ጎሎጎታ ሆነ የመረጠው ሸራ
አሁን እስኪመስል ስቃዩ እያስፈራ
ደም ከደም አረገው አበዛበት ጣር
ብሩሹን አሹሎት እንደጎኑ ጦር
እየወጋ ሳለው በጣም ጨቀነበት
ገብረክርስቶስም ክርስቶስ ላይ ከፋ
የቆዳው አይነቱ በደም ተከልሎ ዘሩ እስከሚጠፋ
እየወጋ ሳለው እየሳለ ወጋው
ዘሩ እስከማይለይ መልኩ ዝም ብሎ
መልኩ ዝም ብሎ ደሙ እስከሚናገር
የትም ያለ ፍቅር እንዳይኖረው ሀገር
እንዳንለው ፈረንጅ እንዳንለው ጥቁር
እንዳንለው ቀይ
በመስቀል ላይ ሞቶ ያየውን ስቃይ
በቆዳ በቀለም እንዳናሳንሰው
በደሙ ተሰቅሎ ሰው ያዳነውን ሰው
ከቀናት ባንዱ ለት ሰዎች ሲማገቱ በቀለሙ ጉዳይ
ሲከራከሩበት
በተመፃዳቂ የምሁራን አንደበት
በአንዱ አፍ ሲጠቁር ባንዱ አፍ ሲነጣ
መታገስ አቃተው ሰዓሊው ተቆጣ
ስሜቱ ገንፍሎ በቡርሽ ጫፍ ወጣ
ሀሳቡን የሚገልፅ ቀለም እስከሚያጣ
ሸራላይ ሰቀለው እንጨት አመሳቅሎ
አልወጣልህ አለው ፍቅርን ስሎ ስሎ
ስሎ ስሎ ስሎ ፍቅርን ስሎ ስሎ
በሳለው እየወጋ በደማው እየቀባ
ክርስቶስ ደሙ እንጂ ዘሩ አልተሰቀም
እንጨቱ ላይ ያለው እውነት ይሄ አይደለም
እያለ እስኪናገር የስዕሉ አንደበት
ገብረክርስቶስም ለክርስቶስ እሚሆን ቀለም እስኪያልቅበት
በነጩ ሸራ ላይ እስከአሁን እሚወርድ ደም አፈሰሰበት
ቀለም ቀይ ቀለም የደም ቀለም የጥላ ቀለም
የሁሉ ነው እንጂ የማንም አደለም
ፍቅር ዘር አይደለም ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ