* እኔ እወድሻለሁ*
ብዙ ሺ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሠለኝ
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ቀኑ እረዘመብኝ
እኔ እወድሻለሁ
የሠማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የአለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ፅጌሬዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደ ሎሚ ሽታ
እንደ እጣን ጢሥ እንጨት
እንደ ከርቤ ብርጉድ
እኔ እወድሻለሁ
አበባ እንዳየ ንብ
እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደሚያሥሠዉ
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሠዉ
ማር ወለላዬ ነሽ ከሸሜላ ሥኩዋር
አማርኛ አይበቃ
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር
እኔ እወድሻለሁ
እንደ ማታ ጀምበር
እንደ ጨረቃ ጌጥ እንደ ንጋት ኮከብ
እኔ የማልጠግብሽ
ስወድሽ- ስወድሽ-ስወድሽ-ስወድሽ
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረዉ
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነዉ
ጣይ እንዳየ ቅቤ
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀዉ
አፈር መሬት ትቢያ ዉሀ እንደሚበላዉ
ፍቅሬ አንቺን ሥወድሽ
ብዙ ሺ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ዉድ እወድሻለሁ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ሥወድሽ ሥወድሽ
እኔ እወድሻለሁ።
ገብረክርስቶሥ ደስታ
ብዙ ሺ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሠለኝ
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ቀኑ እረዘመብኝ
እኔ እወድሻለሁ
የሠማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የአለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ፅጌሬዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደ ሎሚ ሽታ
እንደ እጣን ጢሥ እንጨት
እንደ ከርቤ ብርጉድ
እኔ እወድሻለሁ
አበባ እንዳየ ንብ
እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደሚያሥሠዉ
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሠዉ
ማር ወለላዬ ነሽ ከሸሜላ ሥኩዋር
አማርኛ አይበቃ
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር
እኔ እወድሻለሁ
እንደ ማታ ጀምበር
እንደ ጨረቃ ጌጥ እንደ ንጋት ኮከብ
እኔ የማልጠግብሽ
ስወድሽ- ስወድሽ-ስወድሽ-ስወድሽ
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረዉ
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነዉ
ጣይ እንዳየ ቅቤ
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀዉ
አፈር መሬት ትቢያ ዉሀ እንደሚበላዉ
ፍቅሬ አንቺን ሥወድሽ
ብዙ ሺ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ዉድ እወድሻለሁ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ሥወድሽ ሥወድሽ
እኔ እወድሻለሁ።
ገብረክርስቶሥ ደስታ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ