ረቡዕ 6 ጃንዋሪ 2016

ኢትዮዺያዊ ነኝ
(በእውቀቱ ስዩም)

ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደ አክሱም ግንብ እንደቦሃ አለት
የመከራ እለት ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮዺያዊ ነኝ

ከዋርካ ባጥር ከንቧይ ተልቄ
ከፀሃይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ከምድረ በዳ ውሃ አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በፍን ጠልቄ
ኢትዮዺያዊ ነኝ

ልክ እንደ ቻይናው የትም ሳልረባ
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ
በመጠን ኖሬ አፈር ምገባ
ኢትዮዺያዊ ነኝ

ግትር ጠላቴን ባጭር አንካሴ
እራስ ምታቴን በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
አገር በነገር የማብጠለጥል
ነገር በነገር የማብጠረጥር
ኢትዮዺያዊ ነኝ

እንደ ማህረብ ቤቴን በኪሲ
እንደ ንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤው የምዞር ከቦታ ቦታ
በሰብ ኬላ የማልረታ
ኢትዮዺያዊ ነኝ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ