ረቡዕ 6 ጃንዋሪ 2016

"ክብር ለጠቢባን
ክብር ለደበበ ሠይፉ"

“ ..ደበበ ሰይፉ ሐምሌ 5 ቀን 1942 ዓ.ም. በሲዳሞ፡ ይርጋለም ተወለደ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በይርጋለምና በአዲስ አበባ ኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤቶች ተማረ። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ከፍ ባለ ማዕረግ የመጀመሪያ ድግሪውን አገኘ።
በእንግሊዘኛ ሥነ ጽሁፍ የማስተር ድግሪውን ተቀበለ። ከ1966 እስክ 1984 በረዳት ፕሮፌሰርነት አገለገለ። ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዜዳንት ሆኖ ሰራ። በቀድሞው ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ያልታተሙ መፃህፍት ገምጋሚም ነበር። ። ከተማሪነቱ አንስቶ በርካታ ግጥሞች ጽፏል። «የብርሃን ፍቅር» የተሰኘ የመጀመሪያ የግጥም መድበሉን በ1980 ዓ.ም. በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት አሳተመ። የብርሃን ፍቅር ሁለተኛ ክፍል የሆነውንና ፦ «ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ » የተሰኘውን መድበሉን ደግሞ በ1992 ዓ.ም. በሜጋ አሳታሚ ድርጅት ታተመ። በተውኔቱ ዘርፍ «የቲያትር ጥበብ ከፀሐፌ ተውኔቱ አንፃር» የሚለው መጽሐፉ፤ «ሳይቋጠር የተፈታ» እና «ከባህር የወጣ ዓሣ» የተሰኙት ቲያትሮቹ ይጠቀሳሉ ።
ሚያዝያ 16 ቀን 1992 ዓ.ም. በተወለደ በሃምሳ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሚያዝያ 17 ቀን 1992 ዓ.ም. ንፋስ ስልክ በሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር ቀብሩ ተፈፀመ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ