እሑድ 17 ጃንዋሪ 2016

***ያበጠዉ ይፈንዳ****

አምቄ የቻልኩት በማይችል ጉልበቴ
ከዉሥጤ ያልወጣዉ ምሥጢር የኔነቴ
በልቤ ዉሥጥ ገብቶ የተደላደለዉ
እኔ እንዳልናገር ልሳኔን የዘጋዉ
ከኔና ከአንድዬ ሌላ የማያዉቀዉ
እወቂዉ እንግዲህ ጨክኜ ልግለፀዉ
ያበጠዉ ይፈንዳ ያዉ ያንቻ ፍቅር ነዉ


*** አፍታ ዝምታ***

በዝቶ ከሚነገር የቃላቶች ድርድር
መልሥን ከማይሻ ያላዋቂ መዝሙር
ሥክን እርግት ብላ ከምላሥ ያልወገነች
ከመሥማቷ አብራ ጆሮዋን ያዋሠች
ማዉራትን ማትሻ በምኑም በምኑም
አንድ አፍታ ዝምታ አላት ብዙ ትርጉም

በዳኒ ad


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ