የተዘጋበት ቁልፍ******
የተዘጋን ጓጆ የተቆለፈን በር
የተራበ ሕፃን ለመክፈት ሲታገል
በታላቅ ሰንሰለት የታሰረን አጥር
ማን ዘጋው ? እያለ ጎበዙ ሲያማርር
ሌሊት ይመስለኛል ተኝቼ በሕልሜ
ከአንድ ታላቅ ባህር ከአፋፋ ላይ ቆሜ
የተዘጋውን በር ሊከፍቱት ሲያንኩዋኩ
ተስፋ የቆረጡት ወድቀው በያመስኩ
ተመልክቼ ነበር በትንሽ እድሜዮ
በእንቅልፍ ላይ ባለች ባለች በሕልም ግዜዮ
ለካስ በዛች ሐገር እያንኮኮ ነበር ትውልድ የሚኖረው
እልሁ በርትቶ በሩን እስኪሰብረው
አዎ በዛች ሐገር አባት በልጁ ላይ ቆልፎበት ነበር
በዕዳ በተሰራ በትልቅ ብረት በር
የዛች ምስኪን ሐገር ቁልፉ ግን የጠፋው
እደጅ አልነበረም ውስጥ ጉዋድዋ ነው
እውነት የትኛው ነው ?
ፍሬ ነው አበባ ወይም የፍሬ ግንድ
መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ የሚማገድ
ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሰበረው
ከተጠያቂነት ነፃ የሚባለው ?
እናም በዛች ሐገር መፍትሄ የሚባለው
ቁልፉን ማግኝት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው
እውነት የትኛው ነው?
ፍሬ ነው አበባ ወይም የፍሬ ግንድ
መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ የሚማገድ?
ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሰበረው
ከተጠያቂነት ነፃ የሚባለው ?
አዋ በዛች ሐገር የእናቶች እንባ ሰማያትን ቀዶል
የሕፃናት ጩኧት የእግዛብሔር ዙፋን ስር እንደ ጭቃ ሆኖዋል
አዋ በዛች ሐገር የሚያንኩዋኩ እጆች ቁጥሮች ጨምረዋል
ተስፋ የቆረጡ እርማችን ነው ያሉ ባህር ተሻግረዋል
እኛስ ለምንድን ነው ለዘመን ዘመናት
በሩን የምንመታው ቁልፉን ዘግተውበት
"""በዛች ሐገር እኮ መፍትሔ ሚባለው
ቁልፉን ማግኝት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው"" ::
በኤፍሬም ሥዩም
የተዘጋን ጓጆ የተቆለፈን በር
የተራበ ሕፃን ለመክፈት ሲታገል
በታላቅ ሰንሰለት የታሰረን አጥር
ማን ዘጋው ? እያለ ጎበዙ ሲያማርር
ሌሊት ይመስለኛል ተኝቼ በሕልሜ
ከአንድ ታላቅ ባህር ከአፋፋ ላይ ቆሜ
የተዘጋውን በር ሊከፍቱት ሲያንኩዋኩ
ተስፋ የቆረጡት ወድቀው በያመስኩ
ተመልክቼ ነበር በትንሽ እድሜዮ
በእንቅልፍ ላይ ባለች ባለች በሕልም ግዜዮ
ለካስ በዛች ሐገር እያንኮኮ ነበር ትውልድ የሚኖረው
እልሁ በርትቶ በሩን እስኪሰብረው
አዎ በዛች ሐገር አባት በልጁ ላይ ቆልፎበት ነበር
በዕዳ በተሰራ በትልቅ ብረት በር
የዛች ምስኪን ሐገር ቁልፉ ግን የጠፋው
እደጅ አልነበረም ውስጥ ጉዋድዋ ነው
እውነት የትኛው ነው ?
ፍሬ ነው አበባ ወይም የፍሬ ግንድ
መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ የሚማገድ
ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሰበረው
ከተጠያቂነት ነፃ የሚባለው ?
እናም በዛች ሐገር መፍትሄ የሚባለው
ቁልፉን ማግኝት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው
እውነት የትኛው ነው?
ፍሬ ነው አበባ ወይም የፍሬ ግንድ
መጥፎ ነው ተብሎ ተጥሎ የሚማገድ?
ቁልፉን የጣለው ነው በሩን የሰበረው
ከተጠያቂነት ነፃ የሚባለው ?
አዋ በዛች ሐገር የእናቶች እንባ ሰማያትን ቀዶል
የሕፃናት ጩኧት የእግዛብሔር ዙፋን ስር እንደ ጭቃ ሆኖዋል
አዋ በዛች ሐገር የሚያንኩዋኩ እጆች ቁጥሮች ጨምረዋል
ተስፋ የቆረጡ እርማችን ነው ያሉ ባህር ተሻግረዋል
እኛስ ለምንድን ነው ለዘመን ዘመናት
በሩን የምንመታው ቁልፉን ዘግተውበት
"""በዛች ሐገር እኮ መፍትሔ ሚባለው
ቁልፉን ማግኝት ሳይሆን በሩን መስበር ላይ ነው"" ::
በኤፍሬም ሥዩም
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ