ፕሮፌሰር ሪጃርድ ፓንከረስት አምስት ጠቃሚ እውነታዎች
(የታሪክ ምስክር)
…………///……………
1. ሪቻርድ ፐንክኸርስት እ.ኤ.አ ዲሴምበር 3 ቀን 1927 ዓ/ም ከእንግሊዛዊቷ እናታቸው ሲልቪያ ፓንክኸርስትና ጣሊያናዊ አባታቸው ሲልቮ ኮሮ ተወለዱ። በባንክሮፍት'ስ ስኩል ኢን ውድፎርድ (Bancroft's School in Woodford) ቀዳሚ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ (London School of Economics) የኢኮኖሚካዊ ታሪክ ዶክትሬት አግኙ::
2. የሪቻርድ ፓንክኸርስት እናት ወይዘሮ ሲልቪያ ፓንክኸርስት ከሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ጀምረው የኢትዮጵያ ባህልና ነጻነት ደጋፊ እንደነበሩ በሰፊው ይተረካል። ስለሆነም ህጻኑ ሪቻርድ ብዙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በማወቅ አደጉ። በስተመጨረሻ፣ ሲልቪያ ፓንከኸርስት Ethiopia, a Cultural History የሚለውን መጽሐፋቸውን በ1955 እ.ኤ.አ. ካሳተሙ በኋላ ግፈኛው ፋሺስት ኢጣልያ ተሸንፎ ነጻነታችን ከተመለሰ ወዲህ ጓዛቸውን ጠቅልለው ከልጃቸው ከሪቻርድ ጋር ከ1948 ኑሯቸውን አዲስ አበባ አድርገው «ኢትዮጵያ ኦብዘርቨር» የተሰኘ ወርኃዊ መጽሔት ማሳተም ጀምረው ነበር፡፡ እኝሕ ታላቅ እናት ከጻፏቸው ሃያ መጻሕፍት ስምንቱ በኢትዮጵያ ዙሪያ ያተኮሩ ነበሩ፡፡እመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንሥርዓት ሲጠመቁ ወለተ ክርስቶስ የተባሉ ሲሆን፤ በተወለዱ በ ሰባ ዘጠኝ ዓመታቸው የመስቀል ዕለት መስከረም 17 ቀን 1953 ዓ/ም አርፈው ቀብራቸውም ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከነቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት ባልሥልጣናትና የውጭ ልዑካን በተገኙበት በትልቅ ክብር በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። ቀጥሎም ሪቻርድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥራ ጀመረው በ1962 የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል መስራች ዲሬክተር ለመሆን ሲችሉ Journal of Ethiopian Studies እና Ethiopia Observer የተባሉትን መጽሔቶች ዋና አዘጋጅም ነበሩ።
3. ከአብዮቱ መነሳት በኋላ፣ በ1976 ሪቻርድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለቀው ወደ እንግሊዝ አገር ተሰደዱ። በዚያውም የ School of Oriental and African Studies እና London School of Economics ጥናት ጓድ ከሆኑ በኋላ በ1986 እ.ኤ.አ.፣ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በስደት አቋርጠውት የነበረውን የኢትዮጵያ ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጠሉ።
4. በፋሺስት ወረራ ጊዜ በሙሶሊኒ ትዕዛዝ ከኢትዮጵያ በዘረፋ ተወስዶ በሮማ ከተማ ላይ ቆሞ የነበረውን የአክሱም ሐውልት ወደ ኢትዮጵያ ለማስመልስ የሚደረገውን ጥረት በመምራት 2008 እ.ኤ.አ. ሐውልቱ ወደአክሱም ተመልሶ እንዲተከል አድርገዋል። ለኢትዮጵያ ጥናት ባደረጉት ጥረት የ Officer of the Order of the British Empireን ማዕረግ በ Queen's Birthday Honours ተሸልመዋል
5. ፕሮፌሰር ፓንክኸርስት፣ ባጠቃላይ 400 ጽሑፎችን ለዓለም አቀፍ መጽሔቶች ሲያቀርቡ፣ 22 መጽሓፎችን በትብብር እና 17መጽሓፎችን በራሳቸው ፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ትውፊት ደርሰዋል።
እረጅም እድሜና ጤና ተመኘሁ!!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ