እሑድ 17 ጃንዋሪ 2016

****አገሬን አጣሁዋት****

ዞትር የሚስቁት፣
ወዴት ገቡ አበቦች
የሚፍለቀለቁት
የታሉ ኮከቦች
ምን አጋይቶት ይሆን፤ ሰማይ የከሠለ
ምን ነካው ደመናው ፤ኩበት የመሠለ
አስፋልቱስ የት ሄደ
የተለጠለጠው
ወንዙስ ተሰደደ
ድልድዩስ ምን ዋጠው
የት ተነነ ጫካው
የት መነነ ዋርካው
በለምለም ጣቶቹ፤ሰማይ የሚነካው
ዳበስኩኝ
ፈተሸኩኝ
መረመርሁኝ ካርታ
አገሬን አጣሁዋት፤ ባስቀመጥሁዋት ቦታ፡፡

በእውቀቱ ስዩም


https://fbcdn-sphotos-e-a.akamaihd.net/hphotos-ak-ash2/v/t1.0-9/10922490_318493785012661_6354745148160286841_n.jpg?oh=fbd91824d1b7d8647893ae7cd6a78855&oe=56FF26F5&__gda__=1459714809_5069112532094037e9ea884add2f2915

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ