ዘመን ዘመን ጭኖ ቀን በቀን ተሳፍሮ
ሠልጦ ነጉዶ ሲሄድ ቀናዉ በቀን ኖሮ
እልፍ አይነት ጥበብን ትንግርታዊ ዕዉቀትን
በያኔ አሥተናግዶ ግዜ ሞልታዉ ጓዙን
እርሡ መጥቆ ሢያልፍ ከነ ሙሉ ክብሩ
አንቀላፍቶ ኖሮ ሠዉም በምግባሩ
መለየት አቅቶት እዉቀትን ከሌላዉ
በዉሥጥ ለዉሥጥ ጥቅም አዉርዶ ቢያሠላዉ
ዘር ሀረጉን ቆጥሮ ቢደበላልቀዉ
ያዉ ቀንም መለሠ ሠዉ ተደገፈና
ጊዜ አሳየን ዛሬን ቦርጭ እዉቀት ሆነና
በዳኒ ad
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ