ማክሰኞ 19 ጃንዋሪ 2016

* **የጥምቀት ዉበቱ*** በዳኒ ad

መልካም መልካሙን የምናይበትና የምንሠማበት ሠናይ በዐል
ይሁንላችሁ"

* **የጥምቀት ዉበቱ***

የጥምቀት ዉበቱ
የጥምቀት ድምቀቱ
እሡ ነዉ ምክንያቱ
ፍቅር አንድነቱ
ሥራዉ የወጣቱ!!
ክብር ለሚገባዉ
ክብርን የመሥጠቱ
አይረሴነቱ ተናፋቂነቱ
ለየት የማለቱ
የጥምቀት ዉበቱ
የጥምቀት ድምቀቱ
እሡ ነዉ ምክንያቱ
ፍቅር አንድነቱ
የጎዳናዉ ዉበት
ፃድቃን የሚያልፋበት
ሁሉም በነጭ ልብሥ አምሮና ተውቦ
በአንድነት ሆኖ ቁዱሳንን ከቦ
ሲዘምር ማየቱ
የጥምቀ ት ዉበቱ
የጥምቀት ድምቀቱ
እሡ ነዉ ምክንያቱ
ፍቅር አንድነቱ
ታቦታት ቢያድሩበት
በዝማሬ ብዛት
በምሥጋና ሙላት
አማኞች ሞልተዉት
ይታያል ተዉቦ
ጃንሜዳ እንኳ ጠቦ
የጥምቀት ዉበቱ
የጥምቀት ድምቀቱ
እሡ ነዉ ምክንያቱ
ክብር ለሚገባዉ
ክብር የመሥጠቱ
ፍቅር አንድነቱ
ሥራዉ የወጣቱ
እሡ ነዉ እሡ ነዉ
እሡ ነዉ ዉበቱ
ከብዙዉ ጥቂቱ
የጥምቀት ዉበቱ
የጥምቀት ድምቀቱ
ከጥምቀቱ ገብቶ
በደሥታ ተሻምቶ
ፀበል መረጨቱ
እሡ ነዉ ዉበቱ እሡ ነዉ ድምቀቱ
ደሥታን መሞላቱ ሠላም መሞላቱ
እሡ ነዉ እሡ ነዉ
የጥምቀት ዉበቱ
ፍቅር ና አንድነቱ
እርሡ ነዉ እርሡ ነዉ
የጥምቀት ድምቀቱ
የጥምቀት ዉበቱ

በዳኒ ad

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ